top of page

ነሀሴ 27 2017 - ሆራይዘን አዲስ ጎማን ከሀገር ውስጥ ባለፈ ለጎረቤት ሀገራት ለማቅረብ መታቀዱን ተነገረ፡

  • sheger1021fm
  • Sep 2
  • 1 min read

ሆራይዘን አዲስ ጎማን ከሀገር ውስጥ ባለፈ ለጎረቤት ሀገራት ለማቅረብ መታቀዱን ተነገረ፡፡


ይህን የሰማነው የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ያዘጋጀው አውደርዕይ በተከፈተበት ወቅት ነው፡፡


በአውደርዕዩ 45 በሚድሮክ ኢንቨስትመን ግሩፕ ስር የሆኑ ኩባንያዎች ምርቶቻቸውን አቅርበዋል፡፡


አንዳንድ ኩባንያዎች በእዳ እና በሌሎች ምክንያቶች በሆነ ወቅት ኪሳራ ውስጥ ገብተው ሰራተኞቻቸውን እስከ መበተን ድረስ የሚያሰጋ አደጋ ውስጥ ነበሩ ያሉት የሚድሮክ ኢንቨስትመን ግሩፕ ዋና ስራ አስፈዋፃሚ አቶ ጀማል አህመድ ናቸው፡፡

ree

ሚድሮክ የ5 አመት እቅድ በማውጣት በሰራው ስራ ኩባንያዎች አሁን በጥሩ መንገድ እየሄዱ ነው ያሉት አቶ ጀማል አውደርዕዩም የተዘጋጀው ይህንን ስራ ለማሳየት ነው ብለዋል፡፡


የሆራይዘን አዲስ ጎማ የሽያጭ ኃላፊ አቶ ዘላለም ግርማ በዚህ ዘርፍ አብዛኛው ጥሬ እቃ ከውጪ እንደሚመጣ ይናገራሉ፡፡


አሁን ከአነስተኛ ተሽከርካሪዎች ጀምሮ እስከ ወታደራዊ መኪኖች ድረስ የሚጠቀሙት የመኪና ጎማ ሀገር ውስጥ እያመረቱ መሆኑን አስረድተዋል፡፡


በጎማ ዘርፍ ለመሰማራት የጥሬ እቃ እጥረቱ አንዱ ፈታኝ ችግር ነው ያሉት አቶ ዘላለም 90 ከመቶ የሚሆነው ለጎማ ምርት የሚያገለግለው ጥሬ እቃ ከውጪ ይገባል፡፡


ከተመረተ በኋላም ህብረተሰቡ ለሀገር ውስጥ ምርት ያለው አመለካከት ሌላኛው ፈተና ነው ብለዋል፡፡


ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከአመታዊ ትርፉ ውስጥ 10 ከመቶ የሚሆነው ለማህበራዊ ኃላፊነት እንደሚያውል ተጠቅሷል፡፡


79,000 ሰራተኞች በስሩ የያዘው ሚድሮክ በማዕድን ፣ ግብርና ፣ በሪል ስቴት እና በሌሎችም ዘርፎች የተሰማሩ ኩባንያዎች በስሩ ይገኛሉ፡፡


በረከት አካሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page