top of page

ነሀሴ 22 2017 በአዲስ አበባ ካሉ 1600 የግል ትም/ቤቶች አዲሱን የት/ት ስርዓት የያዘውን መፅሀፍ ግዢ የፈፀሙት 250ዎቹ ናቸው ተባለ

  • sheger1021fm
  • Aug 28
  • 1 min read

በአዲስ አበባ ከተማ ካሉ 1600 የግል ትምህርት ቤቶች ውስጥ አዲሱን የትምህርት ስርዓት የያዘውን መፅሀፍ ግዢ የፈፀሙት 250ዎቹ ናቸው ተባለ፡፡


በ2015 የትምህርት ዘመን ወደ ትግበራ የገባውን #አዲሱን_ስርዓተ_ትምህርት የያዘውን መፅሀፍ አሳትሞ ለመንግስትም ሆነ ለግል ትምህርት ቤቶች የሚያቀርበው የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ነው፡፡


1350ዎቹ የግል ትምህርት ቤቶች መፅሐፍቱን ያልወሰዱት ተማሪዎቻቸውን ሙሉ ለሙሉ መዝግበው ስላላጠናቀቁ መሆኑን ቢሮው ተናግሯል፡፡

ree

በተጨማሪም የግል ትምህርት ቤቶቹ ከመማሪያ መፅሀፍት ውጪ አጋዥ መፅሀፍ ማሰናዳት ቢፈልግ ከቢሮው እውቅናና ማረጋገጫ ማግኘት ግዴታቸው ነው፤ ያንን ካላደረጉ ግን እርምጃ እወስዳለሁ ብሏል፡፡


በዚህም መፅሀፍቱን አሳትሞ ለግል ትምህርት ቤቶች ለሽያጭ ማቅረቡን የተናገረው የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በከተማዋ ካሉ 1600 የግል ትምህርት ቤቶች እስካሁን መፅሀፍቱን የወሰዱት 250 ገደማዎቹ ናቸው ብሏል፡፡


አሁንም ቢሆን ያሳተምኳቸውን መፅሀፍት ትምህርት ቤቶቹ እየወሰዱ ያለው ቢሮው ከዚህ በኋላም ለሚመጡ ትምህርት ቤቶች የተቀመጠላቸው የግዥ ፕሮግራም አለ፤ በዚያ መሰረት መውሰድ ይችላሉ ብሏል፡፡


ፋሲካ ሙሉወርቅ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page