ነሀሴ 21 2017 - የኑሮ ውድነትና የሰላም እጦት መፍትሄ እንዲያገኝ የፓርላማ አባላት በመራጮቻቸው መጠየቃቸው ተናገሩ
- sheger1021fm
- Aug 27
- 1 min read
ያነጋገርናቸው የኦሮሚያ የማዕከላዊ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች ተወካዮች እንደነገሩን ማህበረሰቡ የኑሮ ውድነት ፣ የመሰረተ ልማት ማለትም የመንገድ ፣ የመብራት ፣ የቴሌ እና የውሃ ችግሮች እንዲፈቱለት መጠየቃቸውን ተናግረዋል፡፡
ተወካዮቹ በአገሪቱ ተንቀሳቅሶ ለመስራት የሚያስችል ሰላም እንዲኖር እና ለወጣቱ የስራ እድል እንዲፈጠር ጥያቄ ማቅረባቸው አስረድተዋል፡፡
አባላቱ የመሰረተ ልማት እና የግብርና ግብአት ውድነት መፍትሄ እንዲያገኝ በመራጮቻቸው መጠየቃቸውን አስረድተዋል፡፡
የምክር ቤት አባላቱ መንግስት ማህበረሰቡ እነዚህን በተደጋጋሚ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች እንዲፈታ ጠይቀዋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s





Comments