top of page

ነሀሴ 2 2017 - የፕላስቲክና ጎማ አምራቾች ማህበር፤ የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ድጋፍ እያደረኩ ነው ያለውን ወሬ ሀሰት ነው አለ

  • sheger1021fm
  • Aug 8
  • 1 min read

የኢትዮጵያ ፕላስቲክና ጎማ አምራቾች ማህበር፤ የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አምራቾቹ ሌላ ምርቶችን እንዲያመርቱ ድጋፍ እያደረኩ ነው ያለውን ወሬ ሀሰት ነው አለ፡፡


የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ለእነዚህ አምራቾች ድጋፍ እያደረኩ ነው፤ ከኢኮኖሚውም እንዳይወጡ እያገዝኩ ነው ይላል።


ማህበሩ በበኩሉ ይህ ስራ እንዴት የአካባቢ ባለስልጣን ሊሆን ይችላል፤ ከኢኮኖሚ እንዳይወጡ እየደገፍኩ ነው ማለቱንም አላውቅም ሲል አስረድቷል።


#የኢትዮጵያ_ፕላስቲክና_ጎማ_አምራቾች_ማህበር፤ አብዛኛው የፕላስቲክና ጎማ አምራቾች የኢንዱስትሪ ማሽኖች ሌላ ምርቶችን ተክተው የሚሰሩ አይደሉም እንደውም ከኢኮኖሚው ሙሉ በሙሉ የሚያስወጣ ነው ሲል ተናግሯል፡፡


አዋጁ ወደ ስራ ሲቀየርም በቢሊየን የወጣባቸው የኢንዱስትሪ መሳሪያዎች ለምንም አገልግሎት ስለማይውሉ እጣ ፈንታቸው የሚሆነው አውጥቶ ደጅ መጣል ብቻ ነው ሲል ማህበሩ አስረድቷል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…


ተህቦ ንጉሴ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page