top of page

ነሀሴ 2 2017 - የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ባለፈው ወደ ትግራይ አቅንቶ በነበረበት ወቅት የተነሱለትን ጥያቄዎች በተመለከተ ከፌዴራል መንግስት ጋር ውይይት ለመካሄድ ማቀዱን ተናገረ፡፡

  • Aug 8, 2025
  • 1 min read

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ባለፈው ወደ ትግራይ አቅንቶ በነበረበት ወቅት የተነሱለትን ጥያቄዎች በተመለከተ ከፌዴራል መንግስት ጋር ውይይት ለመካሄድ ማቀዱን ተናገረ፡፡


በትግራይ ክልል ለምክክር አስቻይ ሁኔታ እንዲፈጠር ከፌዴራል መንግስት ጋር በቅርቡ ውይይት ይካሄዳል ተብሏል፡፡


የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በነገው እለት በደቡብ አፍሪካ ከሚገኙት ኢትዮጵያዊያን በፕሪቶሪያ ከተማ አጀንዳ መሰብሰብ እንደሚጀምር ተናግሯል፡፡


ኮሚሽኑ ይሄንን ያለው ያከናወናቸውን ተግባራት በተመለከተ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ ነው፡፡


የኮሚሽኑ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ቃል አቀባይ አቶ ጥበቡ ታደሰ በመስሪያ ቤታቸው በሰጡት መግለጫ ባለፈው የኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች ከትግራይ ክልል ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ማካሄዳቸውን አስታውሰዋል፡፡


የኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ አባላት ከህወሓት ስራ አስፈፃሚ አባላት፣ ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እና ከተለያዩ አካላት ጋር ውይይት ማካሄዳቸው ተነግሯል፡፡


በዚህ ውይይት ላይ የተሳተፉ አካላት በሀይል የተያዙ የትግራይ መሬቶች እንዲለቀቁ ህገ መንግስታዊ ሥርዓቱ ወደ ቀድሞ እንዲመለስ እና መሰል ጥያቄዎች መጠየቃቸውን ያስታወሱት የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ አቶ ጥበቡ ታደሰ በውይይቱ ላይ የተነሱ ጥያቄዎችን በኮሚሽኑ አቅም መፍታት የሚችላቸውን እልባት ለመስጠት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ከኮሚሽኑ አቅም በላይ የሆኑት በተመለከተ ከሚመለከታቸው የፌዴራል ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ለማካሄድ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡


በዚህም በትግራይ ክልል ለምክክር አስቻይ ሁኔታ እንዲፈጠር ለማድረግ ከፌዴራል መንግስት ጋር ይካሄዳል ብለዋል፡፡


በሌላ በኩል የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በነገው እለት በደቡብ አፍሪካ ከሚገኙት ኢትዮጵያዊያን ጋር ውይይት ለማካሄድ በፕሪቶሪያ ከተማ አጀንዳ ማሰባሰብ እንደሚጀምር ኮሚሸኑ ተናግሯል፡፡


የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሰሜን አሜሪካ ከነሐሴ አጋማሽ ጀምሮ የአጀንዳ ማሰባሰብ መድረክ እንደሚያካሂድ የተናገረ ሲሆን በቀጣይ በካናዳ ፣ በእንግሊዝ እና በዱባይ ተመሳሳይ መድረኮችን ለማካሄድ የቅድመ ዝግጅት ስራ እየሰራ መሆኑን ሰምተናል፡፡


እነዚህ መድረኮች አጀንዳ መስጠት የሚፈልጉ ኢትዮጵያዊያን በአገሪቱ ያሉ ችግሮችን መፍትሄ የሚሆኑ አጀንዳዎችን እንዲሰጡ ጥሪ ቀርቧል፡፡


ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Recent Posts

See All
ከህዳሴ ግድብ ከ11 ሚሊዮን ኪሎ ግራም በላይ ዓሣ ተመረተ፡፡

ሐምሌ 21 2018 ከህዳሴ ግድብ ከ11 ሚሊዮን ኪሎ ግራም በላይ ዓሣ ተመረተ፡፡ የዓሣ ምርቱ ወደ መሃል ሃገር እየተጫነ ለአዲስ አበባ ገበያ እየቀረበ ነውም ተብሏል፡፡ ታላቁ የህዳሴ ግድብ መገንባቱን ተከትሎ በተፈጠረው ንጋት ሰው ሰራሽ ሃይቅ በኢትዮጵያ ትልቁና ከ70 በላይ ደሴቶች ያሉት የውሃ አካል ነው፡፡ ከቅርብ

 
 
 
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 30.65 ቢሊዮን ዶላር የሚጠይቅ የኃይል ማስፋፊያ ዕቅድ ይፋ አደረገ።

ሐምሌ 20 2018 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 30.65 ቢሊዮን ዶላር የሚጠይቅ የኃይል ማስፋፊያ ዕቅድ ይፋ አደረገ። እቅዱ የኔትወርክ ማሻሻያ እና ማስፋፊያ፣ የሰብስቴሽን እና ተያያዥ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች፣ ስማርት ግሪድ እና ቆጣሪ ማስፋፋትን እንደሚያካትት አገልግሎቱ ዛሬ ይፋ አድርጓል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page