top of page

ነሀሴ 2 2017 - በትውልድ ኢትዮጵያዊው አቶ አምሳሉ ፀጋዬ ካሣው በአሜሪካ ለአውሮራ ከተማ ም/ቤት አባልነት እጩ ሆነው ቀርበዋል፡፡

  • sheger1021fm
  • Aug 8
  • 1 min read

በትውልድ ኢትዮጵያዊው አቶ አምሳሉ ፀጋዬ ካሣው በ #አሜሪካ ለአውሮራ ከተማ ም/ቤት አባልነት እጩ ሆነው ቀርበዋል፡፡


አቶ አምሳሉ ባለፈው ዓመት በተካሄደው የማሟያ ምርጫ አሸንፈው በአሁኑ ሰዓት የከተማውን ሶስተኛ ከፍተኛ የአስተዳደር ቦታ ይዘዋል፡፡


ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ ከተጓዙ 18 ዓመት እንደሆናቸው የነገሩን አቶ አምሳሉ ባለፉት ዓመታት በተለያዩ የሀላፊነት ቦታዎች በከተማው አገልግለዋል።


ባለፈው ዓመት በአውሮራ ከተማ ለምክር ቤት አባልነት በተካሄደ የማሟያ #ምርጫ ከ37 እጩዎች ጋር ተፎካክረው ማሸነፍ የቻሉ ሲሆን አሁን ከግማሽ ሚሊየን በላይ ነዋሪ በያዘችው የአውሮራ ከተማ የምክር ቤት አባል ሆነው ይሰራሉ።


በአሜሪካ የአሪዞና ግዛት ከ40,000 በላይ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንደሚኖሩ የሚነገር ሲሆን የሚበዙትም መኖሪያቸው አቶ አምሳሉ የምክር ቤት አባል በሆኑበት የአውሮራ ከነማ እንደሆነ ይነገራል።

ree

ኢትዮጵያዊያን ወደ አሜሪካ ፖለቲካ ቀረብ ብለው የመሳተፍ ልምድ ብዙም እንደሌላቸው የነገሩን አቶ አምሳሉ በዚህም ምክንያት ብዙ ተጎድተናል ብለዋል።


በአሜሪካ ልጆች ወልደው የሚያሳድጉ ኢትዮጵያዊያን በብዙ ምክንያት እየተቸገሩ እንደሆነ ተናግረው ወደ ፖለቲካው መቅረቡ በየጊዜው በሚወሰኑ ውሳኔዎች ውስጥ የመሳተፍ እድልን የሚሰጥ ነው ይላሉ።


አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች የኢትዮጵያን እውነት ቀረብ ብለው ለአሜሪካ ባለስልጣናት የሚያስረዱ ሰዎችን ለማግኘትም በአሜሪካ ፖለቲካ ውስጥ መሳተፍ ያስፈልጋል ብለዋል።


ከሶስት ወር በኋላ በሚደረገው የምክር ቤት ምርጫ ላይ እጩ ሆነው የቀረቡት አቶ አምሳሉ በአካባቢው ያሉ ኢትዮጵያዊያን ለምርጫው በመመዝገብ ድምፅ በመስጠት እንዲያግዙ ጥሪ አቅርበዋል።


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…

ቴዎድሮስ ወርቁ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page