top of page

ነሀሴ 19 2017 - ከመስከረም ጀምሮ የተሻሻለው የኤሌክትሪክ ታሪፍ በማህበረሰቡ ቅሬታ እየፈጠረ ነው።

  • sheger1021fm
  • Aug 25
  • 1 min read

ከወርሃ መስከረም ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው አዲሱ #የኤሌክትሪክ_ታሪፍ ማስተካከያ ለቀጣይ 4 ዓመታት በየሶስት ወር ተከፋፍሎ በ16 ጊዜ ተግባራዊ እንደሚደረግ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መናገሩ ይታወቃል፡፡


ይህም አነስተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል መጠን የሚጠቀሙ ደንበኞችን እንዳይጎዳ፣ የኑሮ ደረጃን ያገናዘበና ድጎማን መሰረት ያደረገ ማስተካከያ እንዳደረገም በተደጋጋሚ ሲናገር ሰምተናል።

ree
ree

ነገር ግን ይህ ጭማሬ በብዙዎች የአገልግሎቱ ደንበኞች ዘንድ ቅሬታ እየፈጠረ መሆኑን ነዋሪዎቹ ነግረውናል።


የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በበኩል ተግባራዊ የተደረገው የታሪፍ ማሻሻያ ኑሮ ውድነትን እና የዋጋ ግሽበትን እንዳያባብስ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ደንበኞች የመክፈል አቅም ያገናዘበ እና ድጎማ የሚያርግ ነው ብሏል፡፡


የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማሻሻያ መደረጉ ብቻ ከፍተኛ ጭማሬ አያመጣም ያለው አገልግሎቱ ህብረተሰቡ የሚያነሳው ጥያቄም ካጠቃቀማቸው ጋር ሊገናኝ የሚችል ነው ብሏል።


ከኤሌክትሪክ ታሪፍ ጭማሪው ባለፈ ግን ደንበኞች ወርሃዊ የሀይል ፍጆታ ሂሳባቸውን ሲከፍሉ የአገልግሎት ክፍያ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ለተቆጣጣሪ ባለስልጣን የሚከፈል ቀረጥ እና የቴሌቪዥን የሚከፈል መኖሩን ማወቅ ይኖርባችኋል ብሏል አገልግሎቱ።

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….


ፋሲካ ሙሉወርቅ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page