ነሀሴ 15 2017 - የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት መጪው ምርጫ በወቅቱ እንዲካሄድ የሚያስችል ውይይት ጀምሪያለሁ አለ።
- sheger1021fm
- Aug 21
- 1 min read
ሁሉንም የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያሳትፍ የምርጫ ፍኖተ ካርታ እየተዘጋጀ እንደሚገኝም የምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ሠለሞን አየለ ተናግረዋል።
60 የፖለቲካ ፓርቲዎችን በጋራ የያዘው ምክር ቤቱ እንደ ሀገር ያለውን የሠላም ሁኔታ መገምገሙንም ጠቅሷል።
ሁሉም ሃይሎች ለሠላም ቅድሚያ ሰጥተው እንዲሰሩ ከመግባባት ላይ መደረሱን አቶ ሠለሞን ጨምረው ነግረውናል።
በ2018 ይካሄዳል ተብሎ ለሚጠበቀው ሰባተኛው አጠቃላይ ምርጫ በጀት ከማፀደቅ አንስቶ በተለያዩ ከተሞች የምርጫ ጣቢያ ልየታዎች እያደረግሁ ነው ማለቱ ይታወሳል።
የኔነህ ሲሳይ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s












Comments