top of page

ነሀሴ 15 2017 - ዛሬም ዕድሜያቸው እስከ 17 ዓመት ከሆኑ ኢትዮጵያውያን ህፃናትና ታዳጊዎች 80 በመቶዎቹ የድህነት ህይወት የሚገፉ ናቸው ተባለ።

  • Aug 21, 2025
  • 1 min read

ዛሬም ዕድሜያቸው እስከ 17 ዓመት ከሆኑ ኢትዮጵያውያን ህፃናትና ታዳጊዎች 80 በመቶዎቹ የድህነት ህይወት የሚገፉ ናቸው ተባለ።


የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ከአሜሪካው የጥናት ኢንስቲትዩት እና ከተባበሩት መንግስታት የህፃናት መርጃ ድርጅት ( ዩኒሴፍ ) ጋር በመሆን ያካሄደውን እና የኢትዮጵያውያን ህፃናትን የድህነት ሁኔታ የተመለከተውን ጥናት ውጤት ዛሬ ይፋ አድርጓል።


ጥናቱ ህፃናት የሚያገኙትን እንደ ምግብ፣ ጤና፣ ትምህርት፣ መጠለያ እና ንፅህና ያሉ አገልግሎቶችን በመውሰድ የተካሄደ እንደሆነ ተጠቅሷል።


ውጤቱ በኢትዮጵያ ዕድሜያቸው እስከ 17 ዓመት ከሆኑ ህፃናትና ታዳጊዎች 80 በመቶዎቹ አሁንም በድህነት ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውን አሳይቷል ተብሏል።

በጎርጎሮሳዊያኑ 2018 በተካሄደ ጥናት በኢትዮጵያ የድህነት ህይወት የሚገፉ ህፃናትና ታዳጊዎች 88 በመቶ እንደነበሩ ለትውስታ ተጠቅሷል።


አሁን ላይ ከ88 በመቶ 80 በመቶ እንደቀነሰ ጥናቱ አሳይቷል ተብሏል።


80 በመቶ ድርሻም ግን ትንሽ ስላልሆነ ጉዳዩ ትኩረት ሊሰጠው  ይገባል ሲሉ ጥናቱን ካካሄዱት ሞያተኞች አንዱ እና የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ቃለአብ ከበደ ለሸገር ሬዲዮ ተናግረዋል።


በሃያት ሬጀንሲ ሆቴል ይፋ በሆነው በዚህ የጥናት ውጤት ላይ በህፃናት ዙሪያ የሚሰሩ የተለያዩ የሀገር ውስጥና የውጭ ድርጅቶች ተወካዮች እየመከሩበት ይገኛሉ።


ንጋቱ ረጋሳ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Recent Posts

See All
ዛሬ ብሔራዊ ባንክ ይፋ ባደረገው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ አንድ የአሜሪካ ዶላር በአማካይ በ161 ብር ከ79 ሳንቲም መሸጡ ተነገረ፡፡

ነሐሴ 6 2018 ዛሬ ብሔራዊ ባንክ ይፋ ባደረገው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ አንድ የአሜሪካ ዶላር በአማካይ በ161 ብር ከ79 ሳንቲም መሸጡ ተነገረ፡፡ ዛሬ ይፋ በሆነው ጨረታ 125 ሚሊዮን ዶላር ለጨረታ ቀርቧል ተብሏል፡፡ በጨረታው 28 ባንኮች የተሳተፉ ሲሆን በጨረታው የድርሻቸውን ተጫርተው የወሰዱ ባንኮች ቁጥር 9 መሆ

 
 
 
ብሔርን መሰረት ያደረገው የክልሎች አወቃቀር ይቀጥል በሚለው የ500 ቡድን የሀገራዊ ምክክር ተመካካሪዎች ተስማምተዋል፡፡

ነሐሴ 6 2018 ብሔርን መሰረት ያደረገው የክልሎች አወቃቀር ይቀጥል በሚለው የ500 ቡድን የሀገራዊ ምክክር ተመካካሪዎች ተስማምተዋል፡፡ አገሪቱ የምትከተለው የመንግስት ሥርዓት ምን ይሁን? ለሚለው ተመካካሪዎቹ ኢትዮጵያ በፕሬዚዳንት ትመራ በሚለው ላይ ሙሉ ለሙሉ ተስማምተዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ ከየት ይመረጥ? ሥርዓቱ ፓር

 
 
 
የነሐሴ 6 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች

#ደቡብ_አፍሪካ በደቡብ አፍሪካ በአንድ የማዕድን ዝቃጭ ማስወገጃ ስፍራ መደርመስ 14 ሰዎች የሞቱበት አደጋ እየተመረመረ ነው ተባለ፡፡ ሌሎች 8 ሰዎች ደግሞ አካላዊ ጉዳት እንደገጠማቸው ቢቢሲ ፅፏል፡፡፡ በዝቃጩ ውስጥ የተቀበሩ ሌሎች ሰዎች ሳይኖሩ አይቀሩም ተብሏል፡፡ በአደጋው የሞቱት እና አካላዊ ጉዳት የገጠማቸው ሕ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page