top of page

ብሔርን መሰረት ያደረገው የክልሎች አወቃቀር ይቀጥል በሚለው የ500 ቡድን የሀገራዊ ምክክር ተመካካሪዎች ተስማምተዋል፡፡

  • 7 hours ago
  • 1 min read

ነሐሴ 6 2018


ብሔርን መሰረት ያደረገው የክልሎች አወቃቀር ይቀጥል በሚለው የ500 ቡድን የሀገራዊ ምክክር ተመካካሪዎች ተስማምተዋል፡፡


አገሪቱ የምትከተለው የመንግስት ሥርዓት ምን ይሁን? ለሚለው ተመካካሪዎቹ ኢትዮጵያ በፕሬዚዳንት ትመራ በሚለው ላይ ሙሉ ለሙሉ ተስማምተዋል፡፡


ፕሬዚዳንቱ ከየት ይመረጥ? ሥርዓቱ ፓርላምታዊ ሆኖ ከፓርላማ ይመረጥ? ወይስ ሙሉ በሙሉ ሥርዓቱ ፕሬዚዳንታዊ ሆኖ በህዝብ ቀጥታ ይመረጥ የሚለው ግን ሁሉምን አስማሚ አልሆነም ፡፡


በዚህም በመንግሥት አደረጃጀት እና ቅርፅ በፖለቲካ ሥርዓት፣ ውክልና የምርጫ ሥርዓት ስር ሲመከር የሰነበተው ተመካካሪ ቡድን እነዚህ አጀንዳዎች በልዩነት ወደ ቀጣይ ምዕራፍ እንዲተላለፉ ወስኗል፡፡


የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት ውክልና ምን ይምሰል? የሚለውም ሌላው በልዩነት ያለፈ ንዑስ አጀንዳ ነው ፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ....




ያሬድ እንዳሻው



Recent Posts

See All
ዛሬ ብሔራዊ ባንክ ይፋ ባደረገው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ አንድ የአሜሪካ ዶላር በአማካይ በ161 ብር ከ79 ሳንቲም መሸጡ ተነገረ፡፡

ነሐሴ 6 2018 ዛሬ ብሔራዊ ባንክ ይፋ ባደረገው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ አንድ የአሜሪካ ዶላር በአማካይ በ161 ብር ከ79 ሳንቲም መሸጡ ተነገረ፡፡ ዛሬ ይፋ በሆነው ጨረታ 125 ሚሊዮን ዶላር ለጨረታ ቀርቧል ተብሏል፡፡ በጨረታው 28 ባንኮች የተሳተፉ ሲሆን በጨረታው የድርሻቸውን ተጫርተው የወሰዱ ባንኮች ቁጥር 9 መሆ

 
 
 
የነሐሴ 6 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች

#ደቡብ_አፍሪካ በደቡብ አፍሪካ በአንድ የማዕድን ዝቃጭ ማስወገጃ ስፍራ መደርመስ 14 ሰዎች የሞቱበት አደጋ እየተመረመረ ነው ተባለ፡፡ ሌሎች 8 ሰዎች ደግሞ አካላዊ ጉዳት እንደገጠማቸው ቢቢሲ ፅፏል፡፡፡ በዝቃጩ ውስጥ የተቀበሩ ሌሎች ሰዎች ሳይኖሩ አይቀሩም ተብሏል፡፡ በአደጋው የሞቱት እና አካላዊ ጉዳት የገጠማቸው ሕ

 
 
 
በመንግሥት አደረጃጀት እና ቅርፅ አጀንዳ ሥር ሲመክሩ የቆዩ የሥራ ቡድኖች ከ53 ንዑሳን ጉዳዮች ውስጥ በ50ው ላይ ተስማምተው ወደ ቀጣይ ምዕራፍ ተሻግረዋል።

በመንግሥት አደረጃጀት እና ቅርፅ አጀንዳ ሥር ሲመክሩ የቆዩ የሥራ ቡድኖች ከ53 ንዑሳን ጉዳዮች ውስጥ በ50ው ላይ ተስማምተው ወደ ቀጣይ ምዕራፍ ተሻግረዋል። ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ ተመካካሪ፤ ሦስት ንዑሳን አጀንዳዎች ግን ለአስማሚ ግብረ ኃይል ይላካሉ መባሉን ነግረውናል። ወደ አስማሚ ግብረ ኃይል ይላካሉ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page