ነሀሴ 15 2017 - ''ተቋማት መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆናቸውበጥናትና ምርምር ስራዎች ላይ እንቅፋት ሆነው ቀጥለዋል'' የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት
- sheger1021fm
- 22 minutes ago
- 1 min read
ተቋማት መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆናቸው፣ ሰነዶችን በወጉ ሰንዶ የመያዝ ችግር እና የመሳሰሉት በጥናትና ምርምር ስራዎች ላይ እንቅፋት ሆነው ቀጥለዋል ሲል የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ተናገረ፡፡
በጦርነት የወደሙ ተቋማት መረጃዎች አለመገኘትም ሌላው ችግር ሆኖ ተነሷል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈሪ ጥያሩ ፖሊሲዎችን በሚመለከት ኢንስቲትዩቱ በርካታ ጥናትና ምርምሮችን በማድረግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል ብለዋል።
ይሁን እንጂ ጥናትና ምርምሮች ያለበቂ መረጃዎችና ሰነዶች የማይከወኑ በመሆናቸው ለጥናቱ ግብአት የሚሆኑ መረጃዎችን ከተቋማት ለማግኘት ስንሄድ ለመስጠት ፈቃደኛ አይሆኑም ብለዋል።
እንደ ሀገር የመረጃ አያያዝ እየተሻሻለ ቢሆንም አሁንም ግን በርካታ ተቋማት መረጃዎቻቸውን በወጉ እየሰነዱ አይደለም ይላሉ።
አሉብን ካሏቸው ችግሮች ውስጥ ሌላኛው ደግሞ ጥናቶችን ለመከወኛ የሚሆን የገንዘብ ወይንም የበጀት እጥረት መኖር እና አሁንም በሀገሪቱ የሚስተዋለው የፀጥታ ችግር ይገኝበታል ብለዋል።
የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲቲዩት በየአመቱ በአማካይ 40 ጥናቶችን አከናውኖ እንደሚያጠናቀቅም ሰምተናል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…. https://www.mixcloud.com/ShegerFM/457445s/
ፍቅሩ አምባቸው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
Comments