top of page

ነሀሴ 14 2017 - የአለም ባንክ የኢትዮጵያን የሪል ስቴት ዘርፍ በገንዘብ የመደገፍ ፍላጎት አለኝ ማለቱ ተሠማ።

  • sheger1021fm
  • Aug 20
  • 1 min read

በሌላ በኩል በሪል ስቴት አልሚዎች እና በቤት ገዥዎች መካከል የሚፈጠሩ አለመግባባቶች በድርድር መፍትሄ እንዲያገኙ የሚሰራ የግልግል ዳኝነት ቡድን እየተቋቋመ እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡


በኢትዮጵያ የሪል ስቴት ልማት ከተጀመረ 30 ዓመት ሆኖታል።


በእነዚህ ጊዜያት በርካታ ዜጎች የቤት ባለቤት መሆናቸው፤ የብዙዎች የአኗኗር ዘይቤም መቀየሩ ይጠቀሳል።


የዚያኑ ያህል ዘርፉ ላይ የሚነሱ ችግሮችም አሉ።


አንዱ በሪል ስቴት አልሚዎች የሚሰሩ ቤቶች አነስተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸውን ሰዎች ታሳቢ ያደረጉ አይደሉም፤ ውድ ናቸው የሚል ነው።


የቤቶቹ ዋጋ እነዚህኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ታሳቢ ያደረገ እንዲሆን በተለያዩ አጋጣሚዎች ጥያቄ ሲቀርብ ይሰማል።


ባለፈው ሚያዝያ ወር የተመሰረተው የኢትዮጵያ የሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር ግን የቤቶቹ ዋጋ ውድ ነው በሚለው ሃሳብ አይስማማም።


አቶ ከድር ሰይድ የማህበሩ ዋና ፀሃፊ ሲሆኑ አነስተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች የሪል ስቴት ቤቶች ባለቤት እንዲሆኑ መፍትሄው በአነስተኛ ወለድ ፤ በረጅም ጊዜ የሚከፈል ብድር እንዲያገኙ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ነው ሲሉ ተናግረዋል።


በሪል ስቴት አልሚዎች ላይ የሚቀርበው ሌላው ቅሬታ ባሉት ጊዜ እና የጥራት ደረጃ ቤቶችን ሰርተው አያስረክቡም የሚል ነው።


በዚሁ ምክንያት በአልሚውና እና በደንበኛው መካከል አለመግባባቶች ሲፈጠሩ አንዳንዴም ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ሲያመራ ይታያል።


የተባሉት ችግሮች እንደሚገጥሙ የሚናገሩት ዋና ፀሃፊው አቶ ከድር - የግልግል ዳኝነት አይነት ስራ የሚሰራ ቡድን ማህበሩ እያቋቋመ እንደሚገኝ ነግረውናል።


ማህበሩ በቅርቡ ከአለም ባንክ ተወካዮች ጋር መወያየቱን የነገሩን አቶ ከድር በውይይቱ ባንኩ የኢትዮጵያን የሪል ስቴት ዘርፍ በገንዘብ መደገፍ እንደሚፈልግ ተረድተናል ብለዋል።


የኢትዮጵያ የሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አሁን ላይ 57 አባላት እንዳሉት ሠምተናል።


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..


ንጋቱ ረጋሣ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Recent Posts

See All
ጥቅምት 20 2018 - የፍትህ ስርዓት ችግር ምክንያት ስራው ላይ እክል እየገጠመው መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ተናገረ

የሚሰጣቸውን ምክረ ሃሳቦች ያለ በቂ ምክንያት የማይፈፅሙ ተቋማት በህግ እንዲጠየቁ ለማድረግ ቢሞክርም ባለው የፍትህ ስርዓት ችግር ምክንያት ስራው ላይ እክል እየገጠመው መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ተናገረ፡፡ ተቋሙ የአስተዳደር በደል ደረሰብን እምባችን ይታበስልን የሚሉ አቤት ባዮችን ቅሬታ በመቀበል

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page