ነሀሴ 14 2017 - የሚቀርቡ የሰላም ጥሪዎች ለምን በሚፈለገው ልክ አልሆኑም?
- sheger1021fm
- 26 minutes ago
- 1 min read
መንግስት በፓርቲ ጉባኤዎች ማጠቃለያ መግለጫም ሆነ በተለያዩ መድረኮች በሀገር ሰላም እንዲወርድ ለታጣቂዎች ተደጋጋሚ ጥሪዎችን ቢያቀርብም በሚፈለገው ደረጃ ጥሪው ሰላም ማውረድ አልቻለም፡፡
የ2017 የህዝብ እንደራሴዎችን ምክር ቤት የስራ ዘመን አስመልክተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀስላሴ በበጀት ዓመቱ ብቸኛው ኃይል የመጠቀም መብት ያለው መንግስት ብቻ መሆኑን ጠቅሰው ሰላም በአገሪቱ ለማስፈን መስራት የመንግስት ዋና ጉዳይ መሆኑን ተናግረው ነበር፡፡
ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው መንግስት ለሰላማዊ ንግግር እና ችግሮችን በንግግር ለመፍታትም ዝግጁ መሆኑንም ጠቁመው ነበር፡፡
በርግጥ በየመሃሉ ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪዎች በተለያዩ የሃይማኖት አባቶች፣ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ በሀገር ሽማግሌዎች እና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ቀርበዋል፡፡
በቅርቡም ከሃምሌ 30 እስከ ነሐሴ 02 ቀን 2017 ዓ.ም መደበኛ ስብሰባ አድርጎ ማጠቃለያ መግለጫ ያወጣው የብልጽግና ፓርቲ ምክር ቤትም በመግለጫው ግጭትን ሊያስቀሩ የሚችሉ አማራጮችን ለመሞከር እና በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ለሚፈልጉ ታጣቂዎች ደግሞ አስፈላጊውን ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ተናግሯል፡፡
በእርግጥ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና በአፋር ክልሎች የሰላም ጥሪዎችን የተቀበሉ የታጣቂ ብድኖች መኖራቸውን መንግስት መናገሩ ይታወሳል፡፡
ይህንና ግን የሰላም ጥሪው አሁንም ሙሉ ሆኖ በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ግጭቶች አልቆሙም ፤ ተማሪዎችም ወደ ትምህርት ቤት እንዳልገቡ ፤ ለኗሪም እረፍት መስጠት እንዳልቻለ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በዓመታዊ ሪፖርቱ ጠቁሟል፡፡
የዘርፉ ባለሙያዎች የሰላም ጥሪዎች ውጤት ካላመጡበት ምክንያት የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ለሌሎችም አስተማሪና አጓጊ ሆኖ ያለመተግበሩ ነገር አንዱ ነው ይላሉ፡፡
ለመሆኑ እነዚህ የሰላም ጥሪዎች ለምን ሙሉ በሙሉ ፍሬ ማፍራት ተሳናቸው? ከዚህ በኋላስ ምን ይደረግ? ባለሙያ ጠይቀናል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s