top of page

ነሀሴ 12 2017 - መንግስት ከመጪው መስከረም ወር ጀምሮ ለሰራተኞች የደመወዝ ማሻሻያ እንደሚደርግ ተናገረ

  • sheger1021fm
  • Aug 18
  • 1 min read

በዚህም መሰረት ዝቅተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ ከብር 4,760 ወደ ብር 6,ዐዐዐ ብር ፣ ከፍተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ ከብር 21,492 ወደ ብር 39,000 ብር እንዲሆን ተወስኗል፡፡


የዲግሪ ተመራቂ መነሻ ደመወዝ ደግሞ ከብር 6,940 ወደ 11,500 ብር እንዲያድግ ይደረጋል ብሏል።

ree

የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ይህ ማሻሻያ መንግስትን ተጨማሪ 160 ቢሊዮን ብር የሚጠይቅ እንደሆነ አስረድቷል፡፡


በዚህም ኢትዮጵያ ለደመወዝ የምታወጣው ዓመታዊ ወጪ ወደ 56ዐ ቢሊዮን ብር ያደርሰዋል ተብሏል፡፡


የደመወዝ ጭማሪ ካለው የልማት ፍላጎት አንጻር አገልግሎቶችና መሠረተ ልማት ለማስፋፋት የሚያስፈልገውን ሀብት የሚሻማ ቢሆንም፣ የመንግሥት ሠራተኛውን ኑሮ ማሻሻል ቅድሚያ የሚሰጠው በመሆኑ የተወሰነ ነው ብሏል የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን፡፡


ይሄ የመጨረሻ ማሻሻያ አንዳልሆነ የተናገረው መንግስት በቀጣው ሪፎርሙ እየታየ ጭማሪ የሚደረግ ይሆናል ሲል አስረድቷል፡፡


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page