ዳሸን ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ሸሪክ ከደንበኞቼ በአደራ መልክ የሰበሰብኩትን 16.9 ሚሊየን ብር ለግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ድጋፍ አደረግሁ አለ።
- 4 hours ago
- 1 min read
ሚያዝያ 24/2018
ዳሸን ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ሸሪክ ከደንበኞቼ በአደራ መልክ የሰበሰብኩትን 16.9 ሚሊየን ብር ለግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ድጋፍ አደረግሁ አለ።
30ኛ ዓመቱን ምክንያት በማድረግ ባንኩ ባዘጋጀው ዳሸን ኤክስፖ የማጠናቀቂያ መርሐ ግብር፤ የዳሸን ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ሸሪክ የ8 ዓመት የስኬት ጉዞን አስመልክቶ ማብራሪያ ተሰጥቷል።
በመርሐ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት በዳሸን ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ቺፍ ኦፊሰር አቶ አምዱ ሰማን ባንኩ ጠንካራ የሸሪዓ አማካሪ ኮሚቴ በማቋቋም የማህበረሰቡን ዕሴቶች ያከበሩና ሸሪዓውን የጠበቁ አገልግሎቶች መስጠቱን አጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል።

የዳሸን ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት 'ሸሪክ' ከሚሰጣቸው ዘመናዊና አካታች የባንክ አገልግሎቶች ባሻገር ማህበራዊ ሐላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝም ያነሱት አቶ አምዱ በዛሬው ዕለት ለግብረ-ሰናይ ድርጅቶች የተሰጠው የገንዘብ ድጋፍ የዚሁ ተግባር አንድ አካል መሆኑን አንስተዋል።
ሸሪክ በዚህ ስምንት ዓመት ውስጥ ከ1.5 ሚሊየን በላይ ደንበኞችን ማፍራት እንደቻለ እና ከ25 ቢሊየን ብር በላይ ተቀማጭ ማድረሱን ባንኩ ተናግሯል።
የዳሸን ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት 'ሸሪክ' ከ17 ቢሊየን ብር በላይ የተለያዩ ዘርፎችን ፋይናንስ ማድረግ ችሏልም ተብሏል።
ባንኩ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ሸሪክ አሁን ላይ ከ90 በላይ በሆኑ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነጻ የሆኑ ቅርንጫፎች እና በሁሉም የዳሸን ባንክ ቅርንጫፎቼ በመስኮት በኩል አገልግሎቱ እየተሰጠሁ ነው ብሏል።
ፋሲካ ሙሉወርቅ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7





Comments