top of page

ዘንድሮ 34 የመንገድ ፕሮጀክቶች ግንባታቸው ተጠናቅቆ እንደሚመረቁ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ተናገረ፡፡

  • May 2
  • 1 min read

ሚያዝያ 24/2018

 

ዘንድሮ 34 የመንገድ ፕሮጀክቶች ግንባታቸው ተጠናቅቆ እንደሚመረቁ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ተናገረ፡፡

 

ከ500 በላይ የመንገድ ፕሮጀክሮችን እየሰራ መሆኑን የሚጠቅሰው አስተዳደሩ ከግማሽ በላዩ እየተሰሩ ያለው በሃገር ውስጥ ስራ ተቋራጮች ነው ብሎናል፡፡

 

አንዱና አካባቢ ከሌላው ገጠሩን ከከተማው የሚያገኛኙ የመንገድ ግንባታዎች፣ ጥገናዎችና የዲዛይን ስራዎች እየተሰራባቸው ያሉ ከ500 በላይ ፕሮጀክቶች እንዳሉ የነገሩን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር መሃመድ አብዱራህማን፣ ከእነዚህ መካከል የፈጣን መንገዶችን፣ ክልሎችን እርስ በስርስ የሚያገናኙ፣ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ተነስተው በ5 አቅጣጫ የሚወጡ  ፕሮጀክቶች ናቸው ብለውናል፡፡


ለመሆኑ የኢትዮጵያ የመንገድ ሽፋን ምን ያህል ደርሷል?ያልናቸው ሃላፊው ከ24ዓመታት በፊት 26 ሺህ ኪሎ ሜትር የነበረው የኢትዮጵያ የመንገድ ሸፋን አሁን 180 ሺህ ኪሎ ሜትር ደርሷል፤ከዚህም ውስጥ 30 ሺህ ኪሎ ሜትሩ በፌድራል ደረጃ ያለ ነው ብለዋል፡፡

 


በዘንድሮ ዓመትም በመላው ኢትዮጵያ እየተገነቡ ያሉ 34 የመንገድ ፕሮጀክቶች ስራቸው ተጠናቅቆ ይመረቃሉ ሲሉም ያስረዳሉ፡፡

 

ከዚህ ቀደም የመንገድ ግንባታን ጨምሮ በአጠቃላይ የግንባታው ዘርፍ የስራ ተቋራጮችና አማካሪ መሃንዲሶች በውጭ ምንዛሪ ከሌሎች ሃገራት መጥተው የሚሰሩ ነበሩ የሚሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሃገር ቤት ባለሙያዎቻችን አቅም በብዙ መንገድ እየተገነባ በመሆኑ ከግማሽ በላይ እስከ 55 በመቶ የሚሆኑ ስራዎቻችንን በእነዚሁ ባለሙያዎች ነው የምናሰራው፤እንደውም ሙሉ በሙሉ በራሳችን ባለሙያዎች የመስራት ውጥን አለን ሲሉም ያስረዳሉ፡፡

 

እየተገነቡ ያሉ እነዚህ የመንገድ ፕሮጀክቶች በወሰን ማስከበር ችግሮች፣ በግንባታ እቃዎች መወደድና፣ በግጭቶች ምክንያት ፈተና ውስጥ ቢሆንም ስራቸው ተቋርጦ የነበሩ 14 የመንገድ ፕሮጀክቶችን በዚህ ዓመት ስራቸውን እንደገና ማስጀመሩን መናገሩ ይታወሳል፡፡

 

ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ….

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

YouTube : https://shorturl.at/18TS1                   

Recent Posts

See All
ከአምስት አመት በኋላ በምግብ እጥረት ምክንያት የሚቀነጭሩ ህጻናት እንዳይኖሩ በሰቆጣ ቃል ኪዳን የገባችው ኢትዮጵያ እስካሁን በከወነችው ስራ ምን ውጤት አገኘች?

ሰኔ 15/2018 ከአምስት አመት በኋላ በምግብ እጥረት ምክንያት የሚቀነጭሩ ህጻናት እንዳይኖሩ በሰቆጣ ቃል ኪዳን የገባችው ኢትዮጵያ እስካሁን በከወነችው ስራ ምን ውጤት አገኘች? በ2025 ስራውን በ700 ወረዳዎች ላይ ተግባራዊ አደርጋለሁ ብትልም እዛ ማድረስ ግን አልቻለችም ታዲያ ከ አምስት አመት በኋላ እንደቃሏ

 
 
 
የአሜሪካው የተራድኦ ድርጅት (USAID)ን ጨምሮ የተለያዩ አለማቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ስራቸውን ማቋረጣቸው እና እርዳታ መቀነሳቸው እያሳደረ ያለው ጫና ከፍ ያለ መሆኑ ይነገራል፡፡

ሰኔ 15/2018 የአሜሪካው የተራድኦ ድርጅት (USAID)ን ጨምሮ የተለያዩ አለማቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ስራቸውን ማቋረጣቸው እና እርዳታ መቀነሳቸው እያሳደረ ያለው ጫና ከፍ ያለ መሆኑ ይነገራል፡፡ በእዚሁ ምክንያት የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ግማሽ ያህል ሰራተኞቹን መቀነሱን እና የሰረዘው ፕሮጅክትም መኖሩን መናገ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page