top of page

ነሀሴ 10 2017 - ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የ30 ዓመታት ጉዞውንና የወደፊት ሀሳቡን የሚያሳይበት ዓውደ ርዕይ ማዘጋጀቱን ተናገረ

  • sheger1021fm
  • Aug 16
  • 1 min read

45 ድርጅቶችን በስሩ የሚያስተዳድረው ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የባለፉትን 30 ዓመታት ጉዞውንና የወደፊት ሀሳቡን የሚያሳይበት ዓውደ ርዕይ ማዘጋጀቱን ተናገረ።


ዓውደ ርዕዩም ከነሃሴ 26/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 5 ቀናት በሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድ ተነግሯል።


በዝግጅቱ የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ኩባንያዎች ምርትና አገልግሎቶታቸውን ይዘው ይቀርባሉ፣ የገበያ ትስስር ይፈጥራሉ፣ ለማህበረሰቡም ይሸጣሉ ተብሏል።

ree

ከዚህ በተጨማሪም ሚድሮክ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ ያበረከተው አስተዋጽኦ በተመለከተ በምጣኔ ሀብት አዋቂዎች የፓናል ውይይት እንደሚካሄድ ተነግሯል።


የዓውደ ርዕዩ ዋና አላማም የሜድሮክን ስኬቶች ማሳየት፣ከህዝቡ ጋር ያለውን ግኑኝነትም ለማጥበቅ እንዲሁም የወደፊት እቅዶቹን ማሳወቅ መሆኑ ተጠቅሷል።


45 ኩባንያዎች ያሉት ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በሆቴልና ቱሪዝም፣ በአገልግሎት፣ በኮንስትራክሽን በመሳሰሉት ዘርፎች ይሰራል።


ግሩፑ በየዓመቱ ከሚያገኘው ትርፍ 10 በመቶው ማህበራዊ ሀላፊነቱን ለመወጣት ለተለያዩ ማህበረሰብ አቀፍ አቀልግሎት እንደሚያውለው ተነግሯል።


ንጋቱ ሙሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page