top of page

ነሀሴ 1 2017 - ለፕላስቲክ አምራቾች፤ ድጋፍ እያደረግንላቸው ነው ሲል የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ተናገረ

  • Aug 7, 2025
  • 1 min read

ፕላስቲክ አምራቾች፤ የተከለከሉ የፕላስቲክ ከረጢቶችን የሚተካ ሌላ ምርቶችን እንዲያመርቱ ድጋፍ እያደረግንላቸው ነው ሲል የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ተናገረ።


ባለስልጣኑ ከዚህ ቀደም አንድ ጊዜ ጥቅም ላይ ውለው የሚጣሉ ፕላስቲኮችን የሚያመርቱ ፕላስቲክን የሚተኩ ምርቶች ላይ ቢሰማሩ የኢኮኖሚ ችግር አይገጥማቸውም ብሏል፡፡


በቅርቡ በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የፀደቀው የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ አዋጅ ላይ #የፕላስቲክ_ፋብሪካዎች ይዘጉ፣ ፕላስቲክን ሙሉ በሙሉ አትጠቀሙ የሚል ነገር አልተቀመጠም አዋጁ የከለከለው አንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ ውለው የሚጣሉ የፕላስቲክ ከረጢቶችን ነው ብሏል ባለስልጣኑ።

ባለስልጣኑ ይህን ቢልም የኢትዮጵያ ፕላስቲክ እና ጎማ አምራቾች ዘርፍ ማህበር አንድ ጊዜ ጥቅም ላይ ውሎ የሚጣል የፕላስቲክ ከረጢት የለም ማለቱን ከዚህ ቀደም ዘግበን ነበር።


አቶ ዲዳ ድሪባ የአዲስ አበባ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ናቸው።


በቅርቡ በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የፀደቀው የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ አዋጅ ታትሞ ወደ ባለስልጣኑ ሲመጣ የተደነገጉ ድንጋጌዎችን ለማስፈፀም መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።


በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ ያሉ ብክለቶችን ለመቀነስ እንደ ባለስልጣን መስሪያ ቤት በርካታ ስራዎችን እየከወንን ነው ያሉት አቶ ዲዳ ሆኖም በከተማዋ ለረዥም ዓመት የቆየ ከፍተኛ የብክለት ክምችት በመኖሩ የሚፈለገውን ያህል ውጤት እንዳናመጣ አድርጎናል ብለዋል።


ፍቅሩ አምባቸው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Recent Posts

See All
የነሐሴ 4 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች

#ሳውዲ_አረቢያ በሳውዲ አረቢያ ጂዛን በሚገኝ የነዳጅ ማጣሪያ ላይ ከባድ ቃጠሎ ተቅስቅሶ ነበር ተባለ፡፡ በጂዛኑ ማጣሪያ ላይ ቃጠሎ ተቅስቅሶ የነበረው ከባድ ፍንዳታ ከተሰማ በኋላ እንደሆነ አናዶሉ ፅፏል፡፡ በጁቢየል የተፈጥሮ ጋዝ ማሰናጃ ከተማም ቃጠሎ ተቀስቅሶ ነበር ተብሏል፡፡ የሳውዲ ምንጮች ቃጠሎዎቹ ተቀስቅሰው እ

 
 
 
በሆነውም ባልሆነውም እየተቀጣን ነው ሲሉ አሽከርካሪዎች ያማርራሉ፡፡

ነሐሴ 4 2018 በሆነውም ባልሆነውም እየተቀጣን ነው ሲሉ አሽከርካሪዎች ያማርራሉ፡፡ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት በበኩሉ ሳያጠፋ የምንቀጣው አሽከርካሪ የለም እንዲያውም ሁሉንም ህጎች እናስከብር ብንል የማይቀጣ አሽከርካሪ አይኖርም ብሏል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ.... ምህረት ስዩም

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page