ከዶላር አንፃር የብር የመግዛት አቅም በአንድ ብር ከ 50 ሳንቲም ተጠናከረ፡፡
- 1 hour ago
- 1 min read
ነሐሴ 14 2018
ከዶላር አንፃር የብር የመግዛት አቅም በአንድ ብር ከ 50 ሳንቲም ተጠናከረ፡፡
የኢትዮጵ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ባካሄደው የግማሽ ብሊዮን ዶላር ጨረታ የአንድ ዶላር አማካይ የመግዣ ዋጋ 160 ብር ከ21 ሳንቲም ሆኗል፡፡

ይህም ባለፈው ሳምንት በነበረው ጨረታ አንድ ዶላር ከተሸጠበት 161 ብር ከ75 ሳንቲም አማካይ ዋጋ ጋር ሲነፃፀር ዛሬ የብር መግዛት አቅም መጠነኛ መጠናከር አሳይቷል፡፡
በዛሬው የጨረታ በልዩ ሁኔታ 5 መቶ ሚሊዮን ዶላር የቀረበ ሲሆን የባንኮች ፍላጎት ከ710 ሚሊዮን ዶላር በላይ እንደነበር ከባንኩ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
በጨረታው 22 ባንኮች ተሳትፈው ከአንድ ባንክ ውጪ ሁሉም የተለያየ መጠን ያለው ዶላር እንደገዙም መረጃው ያሳያል፡፡
የዛሬውን ጨምሮ 2 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር በጨረታ ለባንኮች ያቀረበው ብሔራዊ ባንክ የውጪ ምንዛሬ ገብያውን በታቀደው ልክ ማረጋጋት የተቻለ አይመስልመ፡፡
የብር የመግዛት አቅም በየጊዜው እየተዳከመ ሲሆን ጥቁር ገብያውና በመደበኛው የውጭ ምንዛሬ ገብያ መካከል ያለው ልዩነት ከ15 ከመቶ በላይ ሆኖ መቀጠሉ ይነገራል፡፡
ትዕግሥት ዘሪሁን
_edited.jpg)


Comments