top of page

ታህሳስ  23፣2016  - ቡና ባንክ የ"ይቆጥቡ ይሸለሙ" ላይ ለተሳተፉ የዕጣ አሸናፊዎች ሽልማት ሰጠ

 ቡና ባንክ በ3ኛው የ"ይቆጥቡ ይሸለሙ" ፕሮግራም ላይ ለተሳተፉ የዕጣ አሸናፊ መምህራን አና የጤና ባለሞያዎች ሽልማት ሰጠ፡፡

 

በዚህም መሰረት ወ/ሮ ፈጓታዬ ደምሴ የተባሉ የባንኩ ደንበኛ  የቤት አውቶሞቢል አሸናፊ ሆነዋል፡፡

 

ሌሎች አሸናፊዎችም ላፕቶፕ ኮምፒተሮች፣ ታብሌት አና ዘመናዊ የስልክ ቀፎ ተሸልመዋል፡፡

 

ባንኩ  ሶስተኛውን ዙር የመምህራጓና የጤና ባለሞያዎች ይቆጥቡ ይሸለሙ መርኀ-ግብር ለወራት ሲያካሂድ መቆየቱን አስታውሷል፡፡

 

ቡና ባንክ መምህራን እና የጤና ባለሙያዎች በቡና ባንክ በመቆጠብ ላሳዩት  ጥረት አና በቡና ባንክ ቁጠባና ሽልማት ፕሮግራም በመሳተፍ የዕጣ አሸናፊ በመሆቸው የቁጠባ ፕሮግራሙ ተሸላሚ ሆነዋል ብሏል።

 

ባንኩ በተለያዩ የስራ መስኮች የተሰማሩ ሰዎችን ቁጠባን ባህል በማድረግ ህይወታቸውን እንዲያሻሽሉና በሃገር ኢኮኖሚ ግንባታ ላይ የእራሳቸውን ሚና እንዲወጡ  የቁጠባ መርሃ ግብር ዘርግቶ ተግባራዊ እያደረገ እንደሚገኝ ተጠቅሷል።



ከእነዚህም መካከል መምህራን እና የጤና ባለሙያዎች በአበርክቷቸው ልክ ህይወታቸው እንዲሻሻል ባንኩ የአገልግሎቶቹ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችላቸውን የቁጠባ መርሃ ግብር ማሳናዳቱ ተነግሯል።

 

በዚህ የቁጠባ እና ሽልማት መርሃግብር ከመዋዕለ ህጻናት ጀምሮ እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ድረስ በመምህርነት የሚያገለግሉና በትምህርትና ተያያዠ ደጋፊ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ሰዎች እንዲሁም በጤና ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ሃኪሞች፣ ነርሶች፣ ጤና ረዳቶችና ከህክምና ሙያ ጋር ተያያዠነት ያላቸውን አገልግሎት የሚሰጡ ባለሞያዎች ተሳታፊ ሁነዋል ተብሏል፡፡

 


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

 

 

 

bottom of page