top of page

ታህሳስ 17፣2017 - የንብረት ታክስ ትመና የከተሞችን ዓመታዊ ወጪ ፍላጎት ከግምት ውስጥ በማስገባት የሚሰላ ነው ተባለ

  • sheger1021fm
  • Dec 26, 2024
  • 1 min read

የንብረት ታክስ ትመና የከተሞችን ዓመታዊ ወጪ ፍላጎት ከግምት ውስጥ በማስገባት የሚሰላ ነው ተባለ፡፡


ይህ የተባለው በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የፕላን በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ #የንብረት_ታክስ ረቂቅ አዋጅ ላይ በተደረገ ውይይት ወቅት ነው፡፡


የንብረት ታክስ ከሌሎች የታክስ ዓይነቶች የሚለየው ግብር ከፋዩ ይህን ያህል መክፈል እችላለሁ ብሎ የሚያቀርበው ሳይሆን በከተሞች ውሳኔ ተተምኖ ሚሰበሰብ ነው ተብሏል፡፡

ree

ረቂቁ ለቋሚ ኮሚቴው አባላት ያቀረቡት የገንዘብ ሚኒስቴር የህግ ጉዳዮች መመሪያ ኃላፊ አቶ ተወዳጅ መሃመድ ናቸው፡፡


የንብረት ታክስ ( #Property_Tax ) በሊዝ ይዞታ በሚተዳደር መሬት የሚጠቀም መብት ላይ በቤት በህንፃ እንዲሁም በመሬት ማሻሻያ ላይ የሚጣል እንደሆነ አቶ ተወዳጅ አስረድተዋል፡፡


ሌሎች ሀገራት ተንቀሳቃሽ ንብረቶች ላይ የንብረት ታክስን እንደሚጥሉ ያስረዱት ኃላፊው ኢትዮጵያ ግን ተሽከርካሪን ወይም ተንቀሳቃሽ ንብረት ላይ ታክሱን ተግባራዊ እንደማታደርግ አስረድተዋል፡፡


በአዋጁ ለአንድ ሰው መኖሪያነት ሚያገለግል ቤት ታክስ እንደማይደረግ ተነግሯል፡፡


ይህ ግን በአዋጁ በግልፅ አንድ የሰው መኖሪያ ማለት ምን ማለት ነው? የሚለው በግልፅ ትርጓሜ አልተሰጠውም፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…



ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


Recent Posts

See All
ወደ ቀድሞ ቀያቸው ሄደው እንደገና ወደ ደብረብርሃን የተመለሱ ተፈናቃዮች መቸገራቸውን ተናገሩ፡፡ 

ታህሳስ 11/2018   ወደ ቀድሞ ቀያቸው ሄደው እንደገና ወደ ደብረብርሃን የተመለሱ ተፈናቃዮች መቸገራቸውን ተናገሩ፡፡   የአማራ ክልል የአደጋ ስጋት መስሪያ ቤት በጉዳዩ ላይ መልስ ለመስጠት አልፈቀደም።   ከመንግስት የሚቀርበውን ድጋፍ ለተፈናቃዮች የሚያከፋፍለውና ሌሎች ስራዎችን የሚሰራው በመንግስት የተቋቋመ ኮሚ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page