top of page

ባለፈው ዓመት የጥራት ጉድለት አለባቸው ከተባሉት ማዳበሪያዎች ውስጥ 4 መርከብ የሚሆነው ማስመለስ መቻሉን የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ተናገረ፡፡

  • 4 days ago
  • 1 min read

መጋቢት 10/2018


ባለፈው ዓመት የጥራት ጉድለት አለባቸው ከተባሉት ማዳበሪያዎች ውስጥ 4 መርከብ የሚሆነው ማስመለስ መቻሉን የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ተናገረ፡፡


ከዚህ በኋላ ተመሳሳይ ችግር እንዳይገጥም ለማድረግ ከኢትዮጵያ መረጃ ደህንነት አገልግሎት ኢንሳ ጋር አብሮ እየሰራ መሆኑን ኮርፖሬሽን ጠቅሷል፡፡


ከዚህ ቀደም በተቋሙ 5.6 ቢሊዮን ብር በመመዝበር የተቋሙ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በህግ ጥላ ስር መዋላቸው ይታወሳል፡፡


የተቋሙ ኃላፊዎች ሰርተውታል ከተባሉ ጥፋቶች መካከል ጥራቱን ያልጠበቀ ማዳበሪያ ግዢ መፈፀም አንዱ ነበር፡፡


ታዲያ በዚህ ዓመት ይህ ስህተት እንዳይደገም አዲስ አሰራር ስራ ላይ መዋሉን የኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ የሺእመቤት ነጋሽ ነግረውናል፡፡



ባለፈው ዓመት በ2 መርከቦች ላይ ተጭኖ የነበረ የአፈር ማዳበርያ ፍተሻ ሲደረግለት ጥራት ጉድለት ተገኝቶበት ነበር ሲሉም ያስረዳሉ፡፡


አሁን የማዳበርያ ግዢ በቀጥታ ከአምራች ድርጅቶች ጋር ግንኙነት በማድረግ ነው ግዢ እየተፈፀመ ያለው በዚህ ዓመትም የተገዛው የማዳበርያ ግዢ በዚህ መንገድ የተገዛ ማዳበሪያ ወደ ሀገር ቤት እየገባ ነው ብለዋል፡፡


ከዚህ በፊት የነበረው ችግር እንዳይደገም አሰራሮች ወደ ዲጂታል ለመቀየር ከኢትዮጵያ መረጃ አገልግሎት ጋር ስራዎች እየተሰራ ነው ሲሉም ጠቅሰዋል፡፡


ኢትዮጵያ በየአመቱ ከ2. 4 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን በላይ ማዳበርያ ግዢን ታደርጋለች ያሉት ወይዘሮ የሺእመቤት ነጋሽ ለዚህ አመት ከሚያስፈልገው ውስጥ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበርያ ወደ ሀገር ቤት ገብቷል ይላሉ፡፡


ከዚህ በፊት የጥራት ጉድለት ተገኝቶባቸው ከነበሩ ማዳበርያዎች ውስጥ ከሻጮች ጋር በተደረገ ድርድር 4 መርከብ የሚሆነው ጥራቱን ያልጠበቀ ማዳበሪያ መመለስ ተችሏልም ሲሉ ይናገራሉ፡፡


ተቋሙ ከዚህ በኋላ በሚገዙ የማዳበርያ ግዢዎች ከነጋዴዎች ጋር ከመገናኘት ይልቅ ቀጥታ ከአምራቾች ጋር ግንኙነት እንዲፈጠር ይደረጋል በዚህ ዓመትም ስራው ተጀምሯል ተብሏል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..



በረከት አካሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

1 Comment


Tunisha Straub
Tunisha Straub
5 hours ago

Came across Twitter Games and it has a nice collection of casual browser games. The social-oriented games are fun when you want something interactive. Clean layout and quick load times make it easy to jump in.

Like
Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page