በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቦርድ አባላት የሚሾሙለት የስታቲስቲክስ አገልግሎት እንዲቋቋም የሚያዝዝ ረቂቅ አዋጅ ተሰናዳ።
- 9 hours ago
- 2 min read
ሰኔ 1/2018
በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቦርድ አባላት የሚሾሙለት የስታቲስቲክስ አገልግሎት እንዲቋቋም የሚያዝዝ ረቂቅ አዋጅ ተሰናዳ።
ረቂቅ አዋጁ አሁን በስራ ላይ ያለው የስታቲስቲክስ ባለስልጣን መስሪያ ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 442/1997 አንዲሻር ደንግጓል።
የስታትስቲክስ ተቋሙ እንዳዲስ እንዲቋቋም የሚያዘው የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ ረቂቅ አዋጅ ተቋሙ ዘጠኝ የቦርድ አባላት ይኖረዋል ይላል፡፡
ቦርዱም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጠሪ ይሆናል፡፡
ባለፈው ሳምንት ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ.ም ፓርላማው ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ለዝርዝር እይታ ወደ ፕላን፣ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የመራው ረቂቅ ህጉ የስታትስቲክስ ምክር ቤትን በቦርድ የሚተካ ነው።
በስራ ላይ ያለው አዋጅ የስታቲስቲክስ ምክር ቤት የሀገራዊ የስታትስቲክስ ፕሮግራሞችን የማጽደቅ ፣ የመገምገምና ከአስተዳደራዊ መዘገብና ከተለያዩ መዝገቦች የማሰባሰብ ፣ የስታትስቲክስ መረጃ ክምችት በሥርዓት የሚያዝበት ተስማሚ ስልት የመምረጥ ሃላፊነት እንዳለበት ይዘረዝራል።
የሚቋቋመው ቦርድ ደግሞ ዋና ዳይሬክተሩን ሳይጨምር 9 አባላት የሚኖሩት ሲሆን የሚሾሙት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ነው።
ቦርዱ በአባልነት የመንግስት አካላት ፣ የሞያ ማህበራት ፣ የምርምር ተቋማት ፣ የግል ዘርፍ ተወካዮች ፣ የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች እና ታዋቂ ግለሰቦች ያካትታል።
ከተዘረዘሩት ተቋማት የሚመረጡት የቦርድ አባላት ደግሞ በስታቲስቲክስ፣ ኢኮኖሚክስ፣ ሥነ-ሕዝብ ጥናት፣ ዳታ ሳይንስ ወይም ተዛማጅ ዘርፎች የሚገኙ ታዋቂ ባለሞያዎች መሆን አለባቸው ይላል ረቂቁ።
የሚሾሙት የቦርድ አባላት የስራ ዘመን 3 ዓመት ሲሆን ከሁለት የስራ ዘመን በላይ ማገልገል አይችሉም።
የቦርዱ ሰብሳቢና ሌሎች የቦርድ አባላት ደግሞ የሞሾሙት በጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሆነ ተደንግጓል ።
የሃገራዊ የዋጋ ግሽትን ጨምሮ በተለይ የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ መረጃዎችን በመሰብሰብና በመተንተን ሀላፊነት የተሰጠው የስታስቲክስ ተቋም እንዳዲስ የማቋቋሚ አዋጅ የተሰናዳው ከዚህ ቀደም የወጡ የሕግ ድንጋጌዎች አጠቃላይ የብሔራዊ ስታቲስቲክስ ሥርዓትን ሙሉ በሙሉ የሚሸፍኑ ባለመሆናቸው፣ የሥራ መደራረብን ለመቀነስ፣ ተጠያቂነትን ለማጠናከር፣ የአሠራር ቅልጥፍናን ለማሳደግ፣ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሕብረት የመሪነት ሚና መጫወቷን ሁለንተናዊ ከማድረግ አኳያ የተቀናጀ የስታቲስቲክስ ሥርዓት ሕግ አውጥታ ተግባራዊ ማድረጓ ለአህጉራዊ የስታቲስቲክስ ሕጎች ንፅፅር አስፈላጊ በመሆኑ እና የአፍሪካ ስታቲስቲክስ ቻርተር የወጣው አዋጅ ከፀደቀ በኋላ በመሆኑ በአዋጁ ውስጥ ስላልተካተተ እንዲካተት በማስፈለጉ እንደሆነ ተዝርዝሯል፡፡።
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i





Comments