top of page

በጋምቤላ ክልል የተከሰተው ግጭት ተጨማሪ ጉዳት እንዳያደረስ በቂ የጸጥታ አካል ''በአስቸኳይ'' እንዲሰማራ ኢሰመኮ ጠየቀ፡፡

  • sheger1021fm
  • 2 hours ago
  • 1 min read

ታህሳስ 13/2018


በጋምቤላ ክልል የተከሰተው ግጭት ተጨማሪ ጉዳት እንዳያደረስ በቂ የጸጥታ አካል ''በአስቸኳይ'' እንዲሰማራ ኢሰመኮ ጠየቀ፡፡


የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን(ኢሰመኮ) ይህን የጠየቀው በክልሉ የተከሰተውን ግጭት አስመልክቶ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው፡፡


ኮሚሽኑ ከህዳር 28 ጀምሮ በጋምቤላ ከልል ኢታንግ ልዩ ወረዳ፣ በጋምቤላ ወረዳ፣ በጋምቤላ ከተማ እና በዙሪያው ባሉ አካባቢዎች የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ የተፈጸሙ የመብት ጥሰቶችን እየተከታተለ እንደሆነ አስረድቷል።


ኮሚሽኑ የጋምቤላ ከተማ ፖሊስ ጸህፈት ቤት አዛዥ የነበሩት ዋና ኢንስፔክተር ኡሙድ ኡጁሉ መገደልን ተከትሎ በአካባቢው የተኩስ ልውውጥ ሲካሄድ በመቆቱ የሰው ሕይወት እንዲጠፋ፣ አካል እንዲጎድለም ምክንያት ሆኗል ብሏል።


ኮሚሽኑ በመግለጫው የሰዓት ገበድ እላፊ ተጥሏል፤ የመንግስት ተቋማት እና የባንኮች አገልግሎትም ጨምሮ በርካታ አካላት አገልግሎቶች ጨመቋረጣቸውን ተረድቻለሁ ሲል ተናግሯል፡፡


በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች የተፈጠረውን ግጭትና የሰላም መደፍረስ በፍጥነት በማስቆም በሰዎች በሕይወት የመኖር፣ የአካል ደኅንነት፣ ከቦታ ቦታ የመዘዋወር፣ የንብረት፣ የሥራ እንዲሁም ሌሎች ሰብአዊ መብቶች ላይ ተጨማሪ ጥሰቶች እንዳይደርሱ ለመከላከል በቂ የጸጥታ አካላት በአስቸኳይ እንዲሰማሩ እንዲደረግ ኢሰመኮ አሳስቧል።


በጋምቤላ ክልል በተለያዩ ጊዜያት የሚፈጠሩ ግጭቶችን በዘላቂነት ለማስቆም፣ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ እና ወደፊት ተመሳሳይ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እንዳይከሰቱ ለመከላከል የፌዴራሉ እና የክልሉ መንግሥታት ተገቢ እርምጃዎችን ሊወስዱ ይገባል ብሏል ኢሰመኮ።


ኮሚሽኑ አጥፊዎች በህግ እንዲጠየቁም ጠይቋል፡፡


በተለይም በግጭቶችና ጥቃቶች ላይ ተሳታፊ የሆኑ ቡድኖች እና ግለሰቦች ላይ ተገቢውን የወንጀል ምርመራ በማድረግ ተጠያቂነት የማረጋገጥ ጥረቶችን የበለጠ አጠናክሮ መቀጠል እንዲሁም የክልሉ የጸጥታ ተቋማት ግጭቶችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የሚያስችል ብቃት እንዲኖራቸው ማድረግ ይገባል ብሏል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን።

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page