ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ "ሰው ሰራሽ አስተውህሎት ለእድገት" በሚል በአፍሪካ የዲጂታል መሠረተ ልማትን ለማስፋፋት 1 ቢሊዮን ዶላር መመደቧን ይፋ አደረገች።
- sheger1021fm
- 3 minutes ago
- 1 min read
ታህሳስ 13/2018
ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ "ሰው ሰራሽ አስተውህሎት (AI) ለእድገት" በሚል ተነሳሽነት በመላው አፍሪካ የዲጂታል መሠረተ ልማትን ለማስፋፋት 1 ቢሊዮን ዶላር መመደቧን ይፋ አደረገች።
1 ቢሊዮን ዶላሩ በአፍሪካ ሀገራት ለሚካሄዱ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ፕሮጀክቶችን ለማበረታታት እና በገንዘብ ለመደገፍ የሚውል ነው ተብሏል።
ዋና አላማውም የዲጂታል መሠረተ ልማትን በማጎልበት፣ የመንግስት አገልግሎቶችን በማቀላጠፍ እና ምርታማነትን በማሻሻል በአህጉሪቱ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ልማትን ለማበርታት መሆኑ ተጠቅሷል።
የዩናይትድ አረብ ኢምሬትስን ይህንን እቅድ በቅርቡ ተካሂዶ በነበረው የG20 የመሪዎች ጉባኤ ወቅት የተናገሩት የአቡዳቢው ገዥ ሼክ ሞሃመድ ቢን ዛይድ መሆናቸው ተዘግቧል።

ውጥኑ ተግባራዊ የሚሆነው የአቡዳቢ የልማት ፈንድ አካል በሆነው በአቡዳቢ ኤክስፖርት ጽህፈት ቤት (ADEX) ከተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ የውጭ እርዳታ ኤጀንሲ ጋር በመተባበር ነው ተብሏል።
ይህ ትብብር በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት ከላቁ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንዲሁም የሰው ሰራሽ አስተውህሎት ጉልበት እድገታቸውን እንዲደግፉበት ለማስቻል ዩናይትድ አረብ ኤሚሬትስ ያላትን ፍላጎት ያሳየ ነው ተብሏል።
አገሪቱ ይህንን እቅድ ያመጣሁት ታዳጊ ሀገራት ለእድገታቸው እንቅፋት የሆኑባቸውን ጉዳዮችን
የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂዎችን በትምህርት፣ ግብርና እና መሠረተ ልማት በመሳሰሉት ዘርፎች ውስጥ በማካተት እድገትን የሚያፋጥኑ እና የዘላቂ ልማት ዕድሎችን የሚያሰፉ አዳዲስ መፍትሄዎችን እንዲፈጥሩ ለመርዳት አስቤ ነው ብላለች።
ዩናይትድ አረብ ኢሚሬትስ ባለፉት 54 ዓመታት ለአፍሪካ ሀገራት ከ152 ቢሊዮን ዶላር በላይ እርዳታ መስጠቷ ተጠቅሷል።
በአዲሱ የ1 ቢሊዮን ዶላር ሀሳብ አገሪቱ በውጭ እርዳታ ኤጀንሲዋ እና በአቡዳቢ ኤክስፖርት ጽህፈት ቤት በኩል በመላው አፍሪካ AI ተኮር የልማት ፕሮጀክቶችን በመተግበር በአለም ላይ ያላትን የመሪነት ሚናዋን እንድትቀጥል ያስችላታል ተብሏል።
ንጋቱ ሙሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
Telegram : https://t.me/ShegerFMRadio102_1
Facebook፡ https://web.facebook.com/Sheger102.1








