top of page

በጅንካ ከተማ ምንነቱ በመረጋገጥ ላይ ያለ የሄሞራጂክ ፊቨር በሚባል በሽታ 8 ሰዎች መጠርጠራቸውን ተነገረ።

  • sheger1021fm
  • Nov 13, 2025
  • 1 min read

ህዳር 3 2018


በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጅንካ ከተማ ምንነቱ በመረጋገጥ ላይ ያለ የሄሞራጂክ ፊቨር (Hemorrhagic Fever) በሚባል በሽታ 8 ሰዎች መጠርጠራቸውን ጤና ሚኒስቴር ተናገረ።


የጤና ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና ከክልሉ ጤና ቢሮ ጋር በመሆን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተመዘገበውን ይህንን የበሽታ መንስኤ ለማወቅ እና ተጨማሪ ስርጭትን ለመግታት እንዲሁም ለመቆጣጠር ፈጣን ምላሽ ሰጪ ቡድን ወደቦታው በመላክ የመስክ ግምገማዎች እና የላብራቶሪ ምርመራዎችን እያከናወነ መሆኑ ተነግሯል።


በተጨማሪም የማህበረሰብ ቅኝት፣ የንከኪ ልየታ፣የቤት ለቤት ልየታ እንዲሁም የህከምና አገልግሎት አሰጣጥን እያጠናከረ ይገኛል ብሏል።


ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሌላ ተጨማሪ መግለጫ እስከሚሰጥ ድረስ፤ ለመከላከል የሚከተሉትን ምከረ-ሃሳቦች እና ጥንቃቄዎች ተግባራዊ እንድታደርጉ ሚኒስቴር መ/ቤቱ አሳስቧል ፡፡


➡️ በአፍ፣ አፍንጫ እና ሌሎች የሰውነት ከፍሎች የመድማት፣ትኩሳት፣ማስቀመጥ እና ማስመለስ ምልክት ሲኖር ወደ ህክምና ተቋማት መሄድና በወቅቱ የላቦራቶሪ ምርመራ ማድረግ፣


➡️ ምልከት ከታየበት ማንኛዉም ሰዉ ጋር ንክኪ በሚኖርበት ጊዜ ራስን የመከላከያ ዘዴዎችን መጠቀም፣


➡️ ሁልጊዜ እጅን በሳኒታይዘር ወይም በውሃና በሳሙና በመታጠብ ማጽዳት፣


➡️ ማንኛውም ጤና ተቋም በታካሚዎች ልየታ አካባቢ ልዩ ትኩረት በመስጠት የቫይራል ሄሞሬጅክ ፊቨር (Viral Hemmoragic Fever) መሰል በሸታ መለየት፣ መመርመር፣ ማከም እና ሪፖርት ማድረግ ያስፈልጋል ተብሏል።

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page