top of page

በኢትዮጵያ እየተመረተ ካለው የኤሌክትሪክ ኃይል ግማሽ ያህሉ ከህዳሴ ግድብ መሆኑ ተነገረ።

  • 1 hour ago
  • 1 min read

ነሐሴ 7 2018


በኢትዮጵያ እየተመረተ ካለው የኤሌክትሪክ ኃይል ግማሽ ያህሉ ከህዳሴ ግድብ መሆኑ ተነገረ።



በአሁኑ ወቅት የታላቁ ህዳሴ ግድብ በሙሉ አቅሙ ማለትም 5 ሺህ 150 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል እያመረተ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ነግሮናል፡፡


እየተጠናቀቀ ባለው የ2018 ዓመት እንደ ሀገር 38 ሺህ ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል ለማምረት ውጥን ተይዞ 35 ሺህ 671 ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል መመረቱንና፤ከተመረተው ግማሽ ያህሉ ማለትም 18 ሺህ 360 ጊጋ ዋት ሰዓት የተመረተው ከህዳሴ ግድብ መሆኑን የተቋሙ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ነግረውናል፡፡


ከአፍሪካ ግዙፉ የሀይል ማመንጫ የሆነው ግድቡ ኢትዮጵያ የምታመርተውን የኤሌክትሪክ ኃይል መጠን የመጨመሩን ያክል ሃገሪቱ ለሽያጭ የምታቀርበውን የኃይል መጠንም ጨምሮታል የሚሉት አቶ ሞገስ፤


የኃይል ምርቱ ከአምናው በ23 በመቶ መጨመሩን ተከትሎ ከሃይል ሽያጭ የተገኘው ገቢም ከ75 ቢሊዮን ብር በ2018 ዓመት ወደ 121 ቢሊዮን ብር ከፍ ማለቱንም አስረድተዋል፡፡


ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል የማምረት አቅሟ ከዓመት ዓመት እያደገ መምጣቱን የሚናገሩት አቶ ሞገስ፤ ለዚህ ትልቁን ድርሻ የሚይዘው የህዳሴ ግድብ ነው፤ስራው ተጠናቆ ሁሉም ዩኒቶች እየሰሩ መሆኑና ባለፈው ዓመት ግድቡ በቂ ውሃ በመያዙ በሙሉ አቅሙ ማምረት ችሏል ብለዋል።


ይህም የሃገሪቱን ኃይል የማመረት አቅም 9 ሺህ 730 ሜጋ ዋት አድርሶታል ብለውናል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ.....



ምንታምር ፀጋው

Recent Posts

See All
በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ሃዲዶች ላይ ለአካል ጉዳተኞች የተሰራው መወጣጫ(ራምፕ) ለዓመታት በመዘጋቱ አካል ጉዳተኞች ባቡር መጠቀም  ለማቆም ተገደናል ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

ነሐሴ 7 2018 በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ሃዲዶች ላይ ለአካል ጉዳተኞች የተሰራው መወጣጫ(ራምፕ) ለዓመታት በመዘጋቱ አካል ጉዳተኞች ባቡር መጠቀም ለማቆም ተገደናል ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል። የሃዲዱ ጠባቂ የፀጥታ አካላት የተዘጋውን መወጣጫ(ራምፕ) እንዲከፍቱላቸው ቢጠይቁም የተሰጣቸው ምላሽ እስከ ድብደባ የደረሰ

 
 
 
የነሐሴ 7 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች

#ዩጋንዳ ዩጋንዳ ከአውሮፓ የሚባረሩ የ3ኛ አገር ስደተኞችን ልትቀበል ነው ተባለ፡፡ ዩጋንዳ ከአውሮፓ ተባራሪዎቹን ተቀብላ ለማስተናገድ መዘጋጀቷን ካቲሜሪኒ የተሰኘ የግሪክ ጋዜጣ መዘገቡን አናዶሉ ፅፏል፡፡ ጋዜጣው ዘገባውን ያሰራጨው ዲፕሎማሲያዊ ምንጮችን በዋቢነት በመጥቀስ እንደሆነ ታውቋል፡፡ የሐሳቡ ቀዳሚ አፍላቂዎች

 
 
 
በኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች ሊከሰት የሚችለው ኤልኒኖ በግብርና እንዲሁም አምራች እና የአገልግሎት ዘርፎች ላይም ተፅዕኖ ይኖረዋል ተባለ።

ነሐሴ 7 2018 በኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች ሊከሰት የሚችለው ኤልኒኖ በግብርና እንዲሁም አምራች እና የአገልግሎት ዘርፎች ላይም ተፅዕኖ ይኖረዋል ተባለ። ከአስር ዓመት በፊት በኢትዮጵያ የታየው የኤልኒኖ ተፅዕኖ የእህል ምርት ውጤትን ከ15 እስከ 20 በመቶ እንዲቀንስ አድርጎ እንደነበር አንድ የዘርፉ ተመራማሪ ነ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page