top of page

በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ሃዲዶች ላይ ለአካል ጉዳተኞች የተሰራው መወጣጫ(ራምፕ) ለዓመታት በመዘጋቱ አካል ጉዳተኞች ባቡር መጠቀም  ለማቆም ተገደናል ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

  • 2 hours ago
  • 1 min read

ነሐሴ 7 2018


በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ሃዲዶች ላይ ለአካል ጉዳተኞች የተሰራው መወጣጫ(ራምፕ) ለዓመታት በመዘጋቱ አካል ጉዳተኞች ባቡር መጠቀም  ለማቆም ተገደናል ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።


የሃዲዱ ጠባቂ የፀጥታ አካላት የተዘጋውን መወጣጫ(ራምፕ) እንዲከፍቱላቸው ቢጠይቁም የተሰጣቸው ምላሽ እስከ ድብደባ የደረሰ መሆኑንም ቅሬታቸውን ያቀረቡ አካል ጉዳተኞች ነግረውናል፡፡


በከተማዋ ያሉ  የቀላል ባቡር ሃዲዶች ለጉዳት አልባው የደረጃ መወጣጫ፤ለአካል ጉዳተኞች ደግሞ ለዊልቸርና ክራንች ተጠቃሚዎች የተመቸ የመወጣጫ (ራምፕ) እንዳለው የነገሩን ቅሬታ አቅራቢዎቹ፤


ለአካል ጉዳተኛው የተሻለው የትራንስፖርት አማራጭ ባቡር ቢሆንም በዚህ ምክንያት መጠቀም ለማቆም ተገደናል ብለዋል፡፡


የኢትዮጵያ የአካል ጉዳተኞች ብሄራዊ ማህበር የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ተሰማ ሰብስቤ በበኩላቸው ችግሩ ለዓመታት የቀጠለ ነው፤ከአባሎቻችን በሚደርሰን ጥቆማ መሰረት ጉዳዩን ስንመለከተው ችግሩ በጣም ስር የሰደደ ሆኖ አግኝተነዋል ብለውናል፡፡


አካል ጉዳተኞች የትራንስፖርት አማራጭ እንዲያጡ ምክንያት እየሆነ ነው፤ጉዳዩን ለአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት አስረድተን መፍትሄ እንዲሰጡን ብንጠይቅም ሁለት ወራት ሊሞላን ነው፤እናስተካክላለን ብለው ነበር ግን ምንም ምላሽ አላገኘንም ሲሉም ቅሬታቸውን አቅርበዋል፡፡  


የቀረበውን ቅሬታ ይዘን የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑትን ዶክተር ብርሃን አበባውን ምላሽ ጠይቀናል፡፡


መወጣጫው ብዙም ተጠቃሚ ስለሌለውና ሰዎች በዚያ ለመግባት ሲሞክሩ አደጋም እየተፈጠረ ስለነበር 5ዓመት ለተጠጋ ጊዜ ዘግተነዋል ብለዋል።


በአካል ጉዳተኞች ማህበር በኩል ሃያት አካባቢ ስላለው መወጣጫ ቅሬታ ቀርቦልን ለማስተካከል እየሰራን ነው፤ይህንን ያህል ተጠቃሚን እያስተጓጎለ ከሆነ በቂ ጠባቂዎችን በመመደብ መወጣጫውን እንከፍታለን የሚል ምላሽ ሰጥተውናል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ....




ምንታምር ፀጋው

Recent Posts

See All
የነሐሴ 7 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች

#ዩጋንዳ ዩጋንዳ ከአውሮፓ የሚባረሩ የ3ኛ አገር ስደተኞችን ልትቀበል ነው ተባለ፡፡ ዩጋንዳ ከአውሮፓ ተባራሪዎቹን ተቀብላ ለማስተናገድ መዘጋጀቷን ካቲሜሪኒ የተሰኘ የግሪክ ጋዜጣ መዘገቡን አናዶሉ ፅፏል፡፡ ጋዜጣው ዘገባውን ያሰራጨው ዲፕሎማሲያዊ ምንጮችን በዋቢነት በመጥቀስ እንደሆነ ታውቋል፡፡ የሐሳቡ ቀዳሚ አፍላቂዎች

 
 
 
በኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች ሊከሰት የሚችለው ኤልኒኖ በግብርና እንዲሁም አምራች እና የአገልግሎት ዘርፎች ላይም ተፅዕኖ ይኖረዋል ተባለ።

ነሐሴ 7 2018 በኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች ሊከሰት የሚችለው ኤልኒኖ በግብርና እንዲሁም አምራች እና የአገልግሎት ዘርፎች ላይም ተፅዕኖ ይኖረዋል ተባለ። ከአስር ዓመት በፊት በኢትዮጵያ የታየው የኤልኒኖ ተፅዕኖ የእህል ምርት ውጤትን ከ15 እስከ 20 በመቶ እንዲቀንስ አድርጎ እንደነበር አንድ የዘርፉ ተመራማሪ ነ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page