top of page

በአብዛኞቹ አካባቢዎች ላይ ምርጫ ለማድረግ አስቻይ የፀጥታ ሁኔታ መኖሩን በቀረቡ ሪፖርቶች ተረጋግጧል ሲል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተናገረ፡፡

  • 18 minutes ago
  • 1 min read

ግንቦት 10/2018


በአብዛኛዎቹ አካባቢዎች ላይ ምርጫ ለማድረግ አስቻይ የፀጥታ ሁኔታ መኖሩን በቀረቡ ሪፖርቶች ተረጋግጧል ሲል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተናገረ፡፡


አሁንም ግን  ትኩረት የሚሹ ቦታዎች መኖራቸው ተጠቅሷል፡፡


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ  ሥምሪት የሰጣቸው የክትትል ቡድኖች 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚካሄድባቸውን አካባቢዎች የፀጥታ ሁኔታን በተመለከተ ዝርዝር ሪፖትርት ማቅረባቸውን ባወጣው መግለጫ አስረድቷል፡፡


በአካባቢዎቹ ላይ ያለውን ተጨባጭ የፀጥታ ሁኔታና የፖለቲካ ምኅዳር ክትትል አድርጎ ሪፖርት የሚያቀርብ ቡድን ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እንዲሁም ከቦርዱ የተውጣጣ የክትትል ቡድን አዋቅሮ ሥምሪት መስጠቱን ቦርዱ አስታውሷል፡፡


የሥምሪት ቡድኑም ክትትል ሲያደርግ ቆይቶ ሪፖርቱን ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ ለቦርዱና ለባለድርሻ አካላት በልዩ መድረክ አቅርቧል ተብሏል።


በዘጠኝ ቡድን የተዋቀረው የክትትል ቡድን  በመድረኩ ሪፖርቱን ያቀረበ ሲሆን፤ በሪፖርቱም ከፀጥታ ሁኔታ በተጨማሪ የየአካባቢዎቹ የፖለቲካ ምኅዳር፣ ፓርቲዎች በነፃነት ተንቀሳቅሰው የምርጫ ሥራቸውን ለመሥራት ምን ያኽል አስቻይ ሁኔታ አለ የሚለውን፣ ለምርጫው ያለው የሕዝብ ተነሣሽነትና የምርጫ ካርድ አወሳሰድ ሁኔታን ጨምሮ በርካታ የምርጫ ነክ ጉዳዮች መዳሰሳቸው ተጠቅሷል፡፡


በሪፖርቱቶቹ በአብዛኛዎቹ አካባቢዎች ላይ ምርጫ ለማድረግ አስቻይ ሁኔታ መኖሩን የተረጋገጠ ቢሆንም፤ አሁንም ትኩረት የሚሹ ቦታዎች መኖራቸው ተነግሯል።


በየትኞቹ አካባቢዎች ምርጫውን ለማድረግ አስቻይ ሁኔታ እንዳለ፣ የትኖች አካባቢዎች ደግሞ ትኩረት የሚሹ  እንደሆኑ በቦርዱ መግለጫ ላይ አልተጠቀሰም፡፡

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page