top of page

ሰኔ 9 2017 - ሰኔ 10 2017 - የአዲስ አበባ የመጪው ዓመት በጀቷ ከዘንድሮው የ100 ቢሊዮን ብር በላይ ጨመረ።

  • sheger1021fm
  • 11 hours ago
  • 1 min read

የአዲስ አበባ የመጪው ዓመት በጀቷ ከዘንድሮው የ100 ቢሊዮን ብር በላይ ጨመረ።


የአዲስ አበባ ከተማ የ2018 በጀት ዓመት በጀት 350 ቢሊየን ብር እንዲሆን የከተማዋ ካቢኔ ወስኗል።


የካቢኔው ውሳኔ እንዲፀድቅም ለምክር ቤት ተልኳል።


ከበጀቱ ለካፒታል ወጪዎች 249.9 ቢሊዮን ብር ለመደበኛ በጀት ደግሞ 100.1 ቢሊዮን ብር እንዲሆን ታስቧል፡፡

ረቂቅ በጀቱ በዋናነት ለዘላቂ ልማት፣ የስራ እድል ለሚፈጥሩ ትላልቅ  ፕሮጀክቶች እና ከከተማው ነዋሪ በተለያየ መንገድ ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለሚሰጡ አገልግሎትና አቅርቦት የሚውል መሆኑም ተጠቅሷል።


ለአዲስ አበባ ከተማ ለ2017 በጀት ዓመት 230.39 ቢሊዮን ብር ሆኖ መጽደቁ የሚታወስ ሲሆን ተጨማሪ 11 ቢሊዮን ብር ፅድቆ ነበር።


የከተማዋ የ2017  በጀትም ከተጨማሪው ጋር 241.39 ቢሊዮን ሆኖ አመቱ እያለቀ ነው፡፡


በዚህም መሰረት የከተማዋ  የ2018 በጀት ዓመት በጀት ከዘንድሮው የ 108.6 ቢሊዮን ብር ጭማሪ አለው።


የከተማዋ ካቢኔ በዛሬው መደበኛ ስብሰባዉ   የመሬት ወቅታዊ የሊዝ ዋጋ ማሻሻያ አፅድቋል፡፡

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page