top of page

ሰኔ 7 2017 - ራሚስ ባንክ የሞባይል መተግበሪያ እና የካርድ ባንኪንግ አገልግሎቶችን ማስጀመሩን ተናገረ።

  • sheger1021fm
  • Jun 14, 2025
  • 1 min read

መተግበሪያው "ራሚስ ሞባይል አፕ" በማለት የተሰየመ ሲሆን ደንበኞች ቅንጡ ስልካቸውን በመጠቀም ገንዘባቸውን ያለምንም ጊዜ ገደብ እንዲያንቀሳቅሱ፣ ክፍያዎችን እንዲከፍሉ፣ የሞባይል ካርድ እንዲሞሉ እንዲሁም ወደ ቴሌብር ዋሌት ለራሳቸው አሊያም ለፈለጉት ግለሰብ እንዲያስተላልፉ የሚያስችል ነው ተብሎለታል።

የራሚስ ካርድ ባንኪንግ ደግሞ ደንበኞች ባሻቸው ቦታ፣ በፈለጉት ባንክ ኤቲኤም(ATM) ገንዘብ እንዲያወጡ የሚረዳ ሲሆን በተጨማሪም በፈለጉት የፖስ ማሽን በገበያ ማዕከላት በተለያዩ የግብይት ቦታዎች ላይ ክፍያ መፈፀም እንዲችሉ ይረዳቸዋል መባሉን ሰምተናል።


ራሚስ ባንክ ያስጀመራቸው እነዚህ የዲጂታል አገልግሎቶች ደንበኞችን ወደ ዲጂታል ምህዳር የሚመሩና ባንኩ በዲጂታሉ ዘርፍ ያለውን ተሳትፎ ያሳያል ሲሉ የባንኩ ስራ አፈፃሚ አቶ አሊ አህመድ ተናግረዋል።


ራሚስ ባንክ በይፋ ስራ ከጀመረ ገና ሁለት ዓመት የሞላው ቢሆንም በቴክኖሎጂው ዘርፍ ላይ በሰፊው እየሰራ መሆኑን ተነግሯል።


ማርታ በቀለ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…





Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page