top of page

ሰኔ 27 2017 - ስንቄ ባንክ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ያልተጣራ 5 ቢሊየን ብር ማትረፉን ተናገረ

  • sheger1021fm
  • Jul 4, 2025
  • 1 min read

ጠቅላላ ገቢዬም 15.4 ቢሊዮን ብር ነው ብሏል፡፡


በዚህም ባንኩ የ173 በመቶ እድገት ማሳየቱ አስረድቷል፡፡


ባንኩ ይህንን ያለው የ2024/25 የበጀት ዓመት የስራ አፈጻጸሙን በተመለከተ ለመገናኛ ብዙሀን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።


በተጨማሪም ባንኩ ለኢኮኖሚ ዘርፎች ማለትም ለግብርና፣ ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች፣ ለስራ ፈጣሪ ወጣቶች እንዲሁም ለሴቶች የሰጠሁት ጠቅላላ ብድር መጠን የባንክ ለባንክ ብድርን ሳይጨምር 56.7 ቢሊየን ብር ነው ብሏል።


ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር የ102 በመቶ ጭማሬ ማሳየቱን የተናገረው ስንቄ ባንክ ይህ የብድር መጠን ባንኩ ስራ ከጀመረበት የመጀመሪያው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ218 በመቶ እድገት አሳይቷል ተብሏል።

በመደበኛ የባንክና ማይክሮ ፋይናንስ አገልግሎት ከሚሰጠው ብድር በተጨማሪ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር ተግባራዊ አደረኩት ባለው ገቢ የዲጅታል ፋይናንስ አገልግሎት በኩል ያለ ምንም ማስያዣ ባለፉት ሁለት ወራት ብቻ ከ240,000 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች 1.2 ቢሊዮን ብር ብድር አቅርቤያለሁ ሲልም አስረድቷል


የባንኩ ጠቅላላ ካፒታል መጠን ባሳለፍነው በጀት ዓመት ከነበረበት 9.7 ቢሊዮን ብር የ2.7 ቢሊዮን ብር ወይም የ28 በመቶ እድገት ማስመዝገቡ የተነገረለት ሲሆን ጠቅላላ ተቀማጩ ደግሞ 102.5 ብር ደርሷል ሲል ባንኩ ተናግሯል።


590 ቅርንጫፎች እንዳሉትም ባንኩ ጠቅሷል፡፡


81 በመቶ የሚሆነው የባንኩ ቅርንጫፎች የሚገኙት በገጠሪቱ የሀገሪቱ አካባቢ መሆኑም ሲነገር ሰምተናል።

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page