top of page

ሰኔ 26 2017 - ከፋይናንስ ተቋማት የሚሰጠው ብድር በዚህ ዓመት በ75 በመቶ አድርጓል ተባለ፡፡

  • sheger1021fm
  • 11 hours ago
  • 1 min read

ከመካከሉ 80 በመቶው ድርሻ ደግሞ ለግል ዘርፍ የተሰጠ መሆኑን የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ናቸው፡፡


የወጪና ገቢ ንግዷም ከዜሮ በታች ከነበረበት ወጥቶ በ2.6 ቢሊየን ብር መሻሻል ማሳየቱን ተናግረዋል፡፡


ከፋይናንስ ተቋማት ዋናውና ትልቁ ያሉት ባንክ፤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 900 ቢሊየን ብር ያልተመለሰ እዳ እንደነበረበትም አስታውሰዋል፡፡


የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ባይደረግ ኖሮ ባንኩም ሆነ የፋይናንስ ዘርፉ ውድቀት ያጋጠመው ነበርም ብለዋል፡፡


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለመንግስት የልማት ድርጅቶች ሰጥቶ ያልተመለሰለትን 900 ቢሊየን ብር መንግስት እንደወሰደለት ይታወሳል፡፡

በሌላ በኩል የገቢና ወጪ ንግዷም ከነበረበት ጉድለት ወጥቷል ብለዋል፡፡


የወጪ ንግድ 8 ቢሊየን ዶላር መደረሱም ለዚህ ትልቁን እገዛ አድርጓል ተብሏል፡፡


የብድር ጫናውም እንዲቀንስ የተለያዩ ስራዎች እየተከወኑ መሆኑን ጠቅሰው ከአባዳሪዎች ጋር በተደረገ ንግግርና ስምምነት 3.5 ቢሊየን ዶላር አድነናልም ብለዋል፡፡


ያም ሆኖ መንግስት ለተለያዩ ስራዎች እና ግዥ አጠቃላይ ያወጣው ወጭ 1 ነጥብ 2 ትሪሊየን ብር ሲሆን ካገኘው የግብር ገቢ የ300 ቢሊየን ብር ጉድለት እንዳለው ጠቅሰዋል፡፡


ለዚህም ንግድ ፈቃድ ወስደው ግን ግብር የማይከፍሉ 46,000 ያህሉ ግብር እየከፈሉ ባለመሆኑ ነው ይላሉ፡፡


በመሆኑም ንግድ ፈቃድ ወስደው ከሚሰሩት 50 በመቶ ያህሉ እንኳን ግብር እንዲከፍሉ ቢደረግ ኢትዮጵያ የምትሰበስበውን ገቢ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር ያደረጋል ብለው እንደሚያምኑም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡


ትዕግስት ዘሪሁን

Comentários


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page