ሰኔ 24 2017 - ኢትዮጵያን ከውጭ ምንዛሪ ወጭ አድኗል የተባለው የጃፓን ኩባንያ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ስራ ጀምሯል
- sheger1021fm
- Jul 1
- 1 min read
ከዚህ ቀደም ከውጪ ይታተሙ የነበሩ እንደ ቼክ እና ፓስፖርት ያሉ ሚስጥራዊ ህትመቶችን በሀገር ቤት ለማተም፤ ኢትዮጵያን ከውጭ ምንዛሪ ወጭ አድኗል የተባለው የጃፓን ኩባንያ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ስራ ጀምሯል፡፡
የኢንዱስትሪ ፓርኮ ልማት ኮርፖሬሽን ሌሎችም የጃፓን ኩባንያዎች በተለይም በመድሃኒት ማምረች ዘርፍ እንዲሰማሩ ጥሪ እያቀረብኩ ነው ብሏል፡፡
የጃፓን ባለሃብቶች እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በኢትዮጵያ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ምንም ተሳትፎ አልነበራቸውም።
በኢትዮጵያ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ገብቶ ለመስራት የመጀመሪያ የሆነው የጃፓን ኩባንያ ቶፓን ግራቪቲ እንደሚሰኝ ሠምተናል።
ከአንድ ዓመት በፊት ስራ የጀመረው ቶፓን ግራቪቲ እንደ ፓስፖርት እና ቼክ ያሉ ሚስጥራዊ ህትመቶች ላይ እየሰራ እየሰራ ይገኛል ተብሏል።
አሁን ላይ ኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ እንድታድን እያገዘ ነው ሲሉ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን፤ የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን እና ማርኬቲንግ ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዘመን ጁነዲ ተናግረዋል።
በዚህ ዓመት በሃዋሳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ገብቶ መስራት ቶዮ ሶላር ካምፓኒም ሌላው እንደሆነ ሠምተናል።
ኩባንያው ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ ከ25 ሚሊየን ዶላር በላይ ዋጋ ያላቸውን ምርቶች ወደ ውጪ እንደላከ አቶ ዘመን ነግረውናል።
ሚስቲቡሺ የሚባለው ግዙፍ ኩባንያ ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ ገብቶ ለመስራት ፍላጎት አሳይቷል ተብሏል።
ኩባንያው ከሚታወቅበት የመኪና ምርት በተጨማሪ በሌሎች ዘርፎችም እንደሚሰራ አቶ ዘመን ተናግረዋል።
ሠሞኑን በጃፓኗ የኦሶካ ከተማ በነበረው ፎረም ላይም የኮርፖሬሽኑ የስራ ሃላፊዎች በመገኘት ተጨማሪ ባለሃብቶችን ለመጋበዝ ጥረት ማድረጋቸውን ሠምተናል።
በተለይ በመድሃኒት ማምረት መሰማራት ለሚፈልጉ የጃፓን ባለሃብቶች ስላሉ ምቹ ሁኔታዎች ለማስረዳት ሞክረናል ሲሉ አቶ ዘመን ነግረውናል።
ከሰኔ 14 እስከ 19/2017 በኦሶካ የተካሄደውን ፎረም ያዘጋጀው በጃፓን የኢትዮጵያ ኤምባሲ እንደሆነ ሠምተናል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ……
ንጋቱ ረጋሣ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il












Comments