top of page

ሰኔ 23 2017 - የህግ ባለሞያና ጠበቃ አቶ ቴዎድሮስ ጌታቸው የአፍሪካ የጠበቆች ማህበራት ህብረት ም/ቤት ፕሬዘዳንት ሆነው መመረጣቸው ተሰማ

  • sheger1021fm
  • Jun 30
  • 1 min read

በአይቮሪኮስት አቢጃን በተካሄደው 15ኛው የአፍሪካ የጠበቆች ማህበራት ህብረት መደበኛ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያዊው የህግ ባለሞያና ጠበቃ አቶ ቴዎድሮስ ጌታቸው የአፍሪካ የጠበቆች ማህበራት ህብረት ም/ቤት ፕሬዘዳንት ሆነው መመረጣቸው ተሰማ፡፡


የጠበቆች ማህበራት ህብረት ም/ቤት ባካሄደው ስብሰባው አቶ ቴዎድሮስን ለፕሬዘዳንትነት የመረጠው ከአባል ሀገራቱ መካከል ከ3/4ኛ በላይ ድምጽ በማግኘት መሆኑን ሰምተናል፡፡

ree

የአፍሪካ የጠበቆች ማህበራት ህብረት 54ቱን የአፍሪካ ሀገራት በአባልነት የያዘ እና 8 አካባቢያዊ ተቋማትን በአባልነት በመያዝ ግዙፍ የሞያ ማህበር ም/ቤት መሆኑ ይነገራል፡፡


ለመጪዎቹ 3 ዓመታት ም/ቤቱን እንዲመሩ የመረጡት አቶ ቴዎድሮስ ጌታቸው የመጀመሪያው ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆኑ ከምስራቅ አፍሪካ ቀጠናም ፓሉን እንዲመሩ የሆኑ የመጀመሪያው ሰው ናቸው ተብሏል፡፡


በአቢጃን በተደረገው 15ኛው የአፍሪካ የጠበቆች ማህራት ህብረት ም/ቤት ስብሰባ ከፕሬዘዳንቱ በተጨማሪ ሌሎች የስራ አስፈፃሚ አባላትና አምስት ምክትል ፕሬዘዳንቶች ከአፍሪካ የተለያዩ አካባቢዎች መመረጣቸውንም ሰምተናል፡፡


የኔነህ ሲሳይ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…





Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page