top of page

ሰኔ 20 2017 - በአዲስ አበባ ከተማ የደንብ ጥሰት በ69.8 በመቶ ቀንሷል ተባለ።

  • sheger1021fm
  • 1 day ago
  • 1 min read

በሌላ በኩል የደንብ ጥሰቶችን ፈፅመው ከተገኙት ውስጥ ከ300 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ተናገረ።


በአዲስ አበባ የደንብ ጥሰት ከፈፀሙ ሰዎች በተያዘው በጀት ዓመት 11 ወራት የተሰበሰበው ቅጣት ከ300 ሚሊየን ብር በላይ ሲሆን ከግለሰቦች እና ከተቋማት የተሰበሰበ ነው ተብሏል፡፡


ይህንን የሰማነው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የበጀት ዓመቱን እቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና ውይይት ባካሄደበት ወቅት ነው።


በተለይ የኮሪደር ልማቱን እና የወንዝ ብክለትን መቀነስ ላይ ትኩረት ሰጥቼ እየሰራሁበት ነው ያለው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከእነዚህ እና ሌሎች የደንብ ጥሰቶች 397.6 ሚሊየን ብር መሰብሰቡን ተናግሯል።


በበጀት ዓመቱ 11 ወራት ከ3,000 በላይ ህገ-ወጥ ግንባታዎችና አስቁሚያለሁ ያለው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከ38,000 በላይ ህገ-ወጥ ጎዳና ላይ ነጋዴዎችን ቀጥቻለሁ ብሏል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ….

ፋሲካ ሙሉወርቅ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…





Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page