top of page

ሰኔ 17 2017 - ከ23 ቢሊየን ብር በላይ በህግና መመሪያ ውጪ ወጭ ያደረጉ መ/ቤቶች 86 በመቶውን አሁንም ለመንግስት አልመለሱም ተባለ

  • sheger1021fm
  • 20 minutes ago
  • 1 min read

ባለፈው ዓመትና ከዚያም በፊት በፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በተካሄደ የሂሳብ ምርመራ በድምሩ ከ23 ቢሊየን ብር በላይ በህግና መመሪያ ውጪ ወጭ ያደረጉ መ/ቤቶች 86 በመቶውን አሁንም ለመንግስት አልመለሱም ተባለ፡፡


መስሪያ ቤቱ ባካሄዳቸው የሂሳብ ህጋዊነት ምርመራዎች ያላግባብ ወጭ ተደርጎ የተገኘ ከ20 ቢሊዮን ብር በላይ እና በዛሬው የምንዛሪ ዋጋ ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያለው ከ23 ሺህ 230 ዶላር በላይ አድፋፍተው የተገኙ የፌዴራል መ/ቤቶች ገንዘቡን ለመንግስት እንዲመልሱ ታዘው ነበር ተብሏል፡፡


ትዕዛዙን ስለመፈፀማቸው ለማረጋገጥ በ2016 በጀት ዓመት በተደረገው ምርመራ የመለሱት ገንዘብ ከ14 በመቶ እምብዛም እንደማይበልጥ ተነግሯል፡፡

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የ2016 የበጀት ዓመት የፋይናንስ ህጋዊነት እና የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት ዛሬ ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡


የኦዲት ሪፖርቱ እንደሚያሳየው ያለአግባብ ያወጡትን ወይንም ለመንግስት ገቢ ማድረግ ሲገባቸው ሳያስገቡ የቀሩትን በድምሩ ከ23 ቢሊዮን ብር በላይ ገንዘብ መልሱ ከተባሉት መካከል 5 የገቢዎች ሚኒስቴር የቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ፣ 4 የጉምሩክ ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች፣ እንዲሁም ወልቂጤና ሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ ካለባቸው ገንዘብ ከ10 በመቶ ጀምሮ ተመላሽ ያደረጉ ናቸው፡፡


በሌላ በኩል በ2015 እና ከዛ በፊት በነበሩ የበጀት አመታት ከ3.6 ቢሊዮን ብር በላይ በቂ ማስረጃ ሳይቀርብ መ/ቤቶች ወጭ አድርገው መገኘታቸውን ሪፖርቱ ጠቅሷል፡፡


ማስረጃ እንዲያቀርቡ ካልሆነም ገንዘቡን እንዲመልሱ መ/ቤቶቹ ታዘው ነበር፡፡


በ2016 በጀት የሂሳብ ምርመራ ሲደረግም ማስረጃ ካልቀረበለት 3 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር መካከል 1 ነጥብ 9 ቢሊየን ወይንም 54 በመቶው ማስረጃ መቅረቡ በሪፖርቱ ተካቷል፡፡


የኦዲት ሪፖርቱ በ2016 የሒሳብ ምርመራ የክዋኔ ኦዲት ከተደረገባቸው 169 መ/ቤቶች መካከል በጉድለት የታዩትን በዝርዝር የያዘም ነው፡፡


በአዲሱ ኦዲትም በአክሱም ዩኒቨርስቲ እና በ2 የጉምሩክ ቅርንጫፍ መ/ቤቶች ከ3.2 ሚሊዮን ብር በላይ በጥሬ ገንዘብ ጉድለት መገኘቱንና ሌሎችንም ግኝቶችን አካቷል፡፡


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…





Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page