ሰኔ 16 2017 ዛሬ ረፋድ በአዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ9 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡
- sheger1021fm
- Jun 23
- 1 min read
ከሟቾቹ መካከል የ3 ዓመት ዕድሜ ያለው ህፃን የሚገኝበት ሲሆን በ8 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ተናግሯል፡፡
ዛሬ ሰኔ 16 ቀን 2017 ዓ/ም ረፋድ ላይ በግምት 3 ሰዓት ገደማ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 በተለምዶ አባሳሙኤል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ባጋጠመ የተሽከርካሪ አደጋ የሞት እና የአካል ጉዳት ደርሷል ብሏል፡፡
አደጋው የደረሰው ከሃይሌ ጋርመንት ወደ ዩኒሳ አደባባይ ይጓዝ የነበረ የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት አውቶቡስ ከሌላ ሀገር አቋራጭ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ እና መንገድ ስቶ ወደ ተቃራኒ አቅጣጫ በመግባቱ ነው ተብሏል፡፡

አውቶቡሱ ወደ ተቃራኒ አቅጣጫ ከገባ በኋላ ከዩኒሳ አደባባይ ወደ ሃይሌ ጋርመንት ሲጓዝ ከነበረ ዶልፊን ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ በዶልፊኑ ውስጥ ከነበሩት ተሳፋሪዎች መካከል አሽከርካሪውን ጨምሮ የዘጠኝ ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ ጠቅሷል፡፡
ከሟቹቹ መካከል የ3 ዓመት ህፃን እንደሚገኝበትና በሌሎች 8 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል ተብሏል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በአካባቢው ላይ የቆመ እና በጉዞ ላይ የነበረ ሌሎች ሁለት ተሽከርካሪዎች በአውቶቡሱ ጉዳት እንደደረሰባቸው ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments