top of page

ሰኔ 13 2017 - የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን አቶ ዮሐንስ አበራ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አድርጎ ሾመ፡፡

  • sheger1021fm
  • Jun 20
  • 1 min read

ባለፉት ሶስት ዓመታት ተቋሙን በሀላፊነት ሲመሩ የቆዩት አቶ ጌታቸው መንግስቴ የአፍሪካ ሲቪል አቪዬሽን ኮሚሽን የአየር ትራንስፖርት ዘርፍ ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸው ተነግሯል፡፡


አቶ ጌታቸው ከዚህ ቀደም የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ በመሆን ያገለገሉ ሲሆን ወደ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ሀላፊነትም የመጡት ከ13 ዓመት በላይ ተቋሙን በሀላፊነት ሲመሩ የነበሩትን ኮሎኔል ወሰንየለህ ሁነኛውን ተክተው ነበር፡፡


የተቋሙ አዲሱ ዋና ዳይሬክተር በመሆን የሾሙት አቶ ዮሐንስ አበራ በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ከአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪነት አንስቶ በተለያዩ ሀላፊነት ሰርተዋል፡፡


ወደ አዲስ ሀላፊነታቸው ከመምጣታቸው በፊትም የአየር ትራፊክ ማኔጅመንት ዳይሬክተር ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡


ቴዎድሮስ ወርቁ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…





Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page