ሰኔ 12 2017 - ቀርጫንሼ ግሩፕ የቡና ምርታማነት ለማሳደግ ከዲላ ዩኒቨርስቲ ጋር በትብብር ለመስራት ተስማማ
- sheger1021fm
- 18 hours ago
- 1 min read
በዓመት 65 ሚሊዮን ኪሎ ግራም ቡና ለአለም ገበያ እያቀረበ መሆኑንን የተናገረው ቀርጫንሼ ግሩፕ የቡና ምርታማነት ለማሳደግ ከዲላ ዩኒቨርስቲ ጋር በትብብር ለመስራት ተስማማ፡፡
ስምምነቱንም የቅርነጫንሼ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚና ባለቤት እስራኤል ደገፋ (ዶ/ር) እና የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ኤሊያስ አለሙ(ዶ/ር) ተፈራርመዋል፡፡
ስምምነቱ በሽታና ድርቅና የሚቋቋሙ የቡና ዝርያዎችን በማውጣት ምርትና ምርታማነት ለመጨመር ያለመ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ቡና እንደ ሀገር በሄክታር ከ8 እስከ 10 ኩንታል ይገኝ እንደነበር ያስታወሰው ቀርንጫንሼ ግሩፕ ቡናን በጠብታ መስኖ ያለ ጥላ በማልማት በሄክታር 60 ኩንታል ማግኘቱን ተናግሯል፡፡
ከጂማ ዩኒቨርሲቲ ጋር የተደረገው ስምምነትም ይህንን ከፍ ለማድረግ ፤ ገበሬውንም ሀገርንም ለመጥቀም ያግዛል ተብሎለታል፡፡
ቀርጫንሼ በአመት 65,000 ቶን ቡና ለአም ገበያ እያቀረበ እንደሆነ የነገሩን የድርጅቱ የግብርና ስራዎች ዳይሬክተር ወንድይፍራው ተፈራ (ዶ/ር) አስረድተዋል፡፡
ዲላ ዩኒቨርሲቲ በ30ኛ ዓመት ዋዜማ ላይ መሆኑንን የተናገሩት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ኤሊያስ አለሙ(ዶ/ር) ዩኒቨርሲቲው በቡና አብቃይነቱ የሚታወቅ አካባቢ እንደመሆኑ ትብብሩ ለገበሬውም ለቀርጫንሼ የተሻሻሉ የቡና ዝርያዎችን ለማውጣት ያግዛል ብለዋል፡፡
የቀርንጫንሼ ግሩፕ ባለቤትና ዋና ስራ አስፈፃሚ እስራኤል ደገፋ(ዶ/ር) ድርጅታቸው የአለም አቀፍ የቡና ምርመራ ማዕከልን ጨምሮ ከሌሎች የምርመራ ድርጅቶቻ ጋር የቡና ምርታማነት ለማሳደግ ሲሰሩ መቆየታቸውን አስታውሰዋል፡፡
ከዲላ ዩኒቨርሲቲ ጋር የተደረገው ስምምነትም ይህንን ስራ ያበረተዋል ብለዋል፡፡
ከዲላ ዩኒቨርሲቲ ጋር በቡና ልማት አብሮ ለመስራት የተፈራረመው ቀርጫንሼ ግሩፕ ከግብርናው በተጨማሪ በማኑፋክቸሪንግ፣ በሆቴልና ቱሪዝም፣ ግንባታ፣ አስመጪና ላኪነት በመሳሰሉት ዘርፎችም እየሰራ እንደሆነ ሲነገር ሰምተናል፡፡
ንጋቱ ሙሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments