top of page

ሰኔ 10 2017 - የኤሌክትሪክ ሀይል ስርቆት የፈፀሙ እስከ አንድ ሚሊዮን ብር የሚቀጡበት መመሪያ ስራ ላይ ዋለ

  • sheger1021fm
  • Jun 17
  • 1 min read

በተሻሻለው መመሪያ መሰረት የሀይል ስርቆት የፈፀመ መኖሪያ ቤት ወይም ግለሰብ 20,000 ብር ይቀጣል ተባለ።


የከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች ለሚፈፅሙት የሀይል ስርቆት ደግሞ 1 ሚሊየን ብር ቅጣት እንደሚጣልባቸው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናገረ።


በበጀት ዓመቱ 11 ወራትም 298 ደንበኞቹ የኤሌክትሪክ ሀይል ስርቆት መፈፀማቸውን አገልግሎቱ እወቁልኝ ብሏል፡፡


ይህም በገንዘብ ሲሰላ 259 ሚሊየን ብር ኪሳራ እንዲደርስብኝ አድርጓል ብሏል።


ከዚህ ቀደም የሀይልም ሆነ የመሰረተ ልማት ስርቆት የሚፈፅሙ ደንበኞችን የሚቀጣ የህግ ማእቀፍ ቢኖርም ዝርዝር የማስፈፀሚያ ደንብ እና መመሪያ አለመኖሩ ለመሰረተ ልማቶቹ የሚደረግ ጥበቃ ክፍተት እንዲኖረው አድርጓል።

ree

በተጨማሪም ወንጀለኞቹ ላይ አስተማሪ ቅጣት ሲጣልባቸው አለመታየቱ ችግሩ እንዲጨምር ከሚያደርጉ ምክንያች መካከል መሆኑን የተናገረው አገልግሎቱ በዚህም ምክንያት የሀይል ስርቆትን የፈፀሙ ደንበኞች ሲዳኙበት የነበረው ህግ መከለሱን እና ወደ ስራ መግባቱን ተናግሯል።


በዚህም አገልግሎቱ ፈትኖኛል ያለውን የሀይል ስርቆት ለመቀነስ ተሻሽሏል ባለው መመሪያ መሰረት የሀይል ስርቆት ፈፅሞ የተገኘ የንግድ ቤት 500 ሺህ ብር፣ የዝቅተኛ ኢንዱስትሪ 750 ሺህ ብር ቅጣት ይጣልባቸዋል ተብሏል።


የከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች ለሚፈፅሙት የሀይል ስርቆት 1 ሚሊየን ብር ቅጣት እንደሚጣልባቸው የተነገረ ሲሆን ለመኖሪያ ቤት ደግሞ 20 ሺህ ብር ተጥሏል ብሏል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት።


ደንበኞች ከዚህ ቅጣት በኋላ በድጋሜ የሀይል ስርቆት የሚፈፅሙ ከሆነ ደግሞ የመጀመሪያ ቅጣታቸውን በእጥፍ እንዲከፍሉ ይደረጋል መባሉን ሰምተናል።


ፋሲካ ሙሉወርቅ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…





Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page