ሬፍሌክስሎጂ (Reflexology) ምንድነው?
- Nov 14, 2025
- 2 min read
ሬፍሌክስሎጂ (Reflexology) ምንድነው?
በጥንታዊ ግብጻውያን ፣ ቻይና እና ህንድ ውስጥ በባህላዊ መንገድ እንደተጀመረ የሚነገርለት ሬፍሌክስሎጂ በ1900 በተደረገ ጥናት መሰረት የውስጥ እግር ላይ እያንዳንዱን የሰውነትን ክፍልን የሚወክል ነርቭ እንዳለ በሳይንስ ተረጋግጧል ይላሉ።
ሬፍሌክስሎጂ (Reflexology) በእግር ፣ በእጅ መዳፍ እና በጆሮ አከባቢ የሚገኙ የነርቭ ጫፎችን በማሸት የተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ጋር የሚደርስ በሳይንስ የተረጋገጠ አጋዥ ህክምና እንደሆነ የሬፍሌክስሎጂ ባለሙያ የሆኑት ብርሃኑ ጣሰው ይናገራሉ።
ሳይንሱ እንደ ደም ግፊት ፣ ካንሰር ፣ ስኳር የመሳሰሉ ክሮኒክ ካልሆኑ በሽታዎች በስተቀር ሬፍሌክስሎጂ ከ8 እስከ 12 ዙር ቢታሹ እንደሚመክር አስረድተው ደም ግፊት ያለበት ሰው ግን አንገቱ አከባቢ ጫና ፣ ራስ ምታት ፣ ጭንቀት እና ሌሎችም በበሽታው ምክንያት የሚመጡ ተጓዳኝ ችግሮችን በሬፍሌክስሎጂ መዳኒቱን በማገዝ መቀነስ እንደሚቻል ጠቁመዋል።

እንዲሁም የነርቭ ጫፍ በሚታሽበት ጊዜ የራስ ምታት ፣ የእንቅልፍ ችግር ፣ ማይግሪን ፣ ጭንቀት እና ሌሎችም በሽታዎችን ማስታገስ አንዳንዴም ማጥፋት እንደሚቻል ገልጸው እንደ ጨጓራ ፣ ሳንባ ፣ ኩላሊት ፣ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን እና ሳይነስ የእግር መዳፍ ላይ የሚገኙ የነርቭ ጫፎች በሚታሹበት ጊዜ ወደ ዋናው የሰውነት ክፍል መልዕክት በማድረስ ስለሚነቃቁ በተፈጥሯዊ መንገድ ሰውነታችን እራሱን በራሱ እያከመ ወደ መጀመሪያው ጤንነት መመለስ የሚቻልበት የህክምና አይነት እንደሆነ ብርሃኑ ጣሰው ይናገራሉ።
ሬፍሌክስሎጂ እራሱን የቻለ አንድ አጋዥ ህክምና እንደሆነ ሳይንሱ ቢያረጋግጥም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን አንድ እራሱን የቻለ የህክምና አይነት እንደሆነ በስራ ቆይታዬ ያስተዋልኩ ስለሆነ በደንብ ጥናት ቢደረግበት እራሱን የቻለ አንድ ህክምና መሆን እንደሚችልም ጠቁመዋል።
በባህላዊም በዘመናዊም መንገድ ትልቅ አስተዋጽዎ እንዳለውም አስረድተው በተለይ በዘመናዊው መንገድ የመዳፍ ነርቮችን ማፕ በማንበብ የሚታሸው እያንዳንዱ ቦታን በማወቅ ቴክኒካል በሆነ መንገድ እውቀት ባለው በባለሙያ ነው ብለዋል።
በባህላዊ መንግድ በተለይ በክፍለሀገር አከባቢ እንግዳ ሲመጣ እግር ሲታጠብ በዛው በደንብ እንደሚታሽና የውስጥ እግር ሲታሽ ሙሉ የሰውነት ክፍል እንደሚነቃቃም ጠቁመዋል።
በሌላ አለም በጣም የተለመደ ህክምና ሲሆን ሰው እየተዝናና ህክምና የሚያገኝበት እንደሆነ ተናግረዋል። እኛ ሀገር ግን ብዙ ያልተለመደ እና ከባዱን እስቴጅ ከተጨረሰ በኋላ መጨረሻ ላይ ወደ ሬፍሌክስሎጂ እንደሚመጣ ጠቁመዋል።
ከትልቁ ወደ ትንሽ ሳይሆን ከትንሹ ወደ ትልቁ መሄድ መለመድ ስለሚያስፈልግ በቅድሚያ ሬፍሌክስሎጂ ቢጀምር መፍትሔው ሊገኝ ይችላል። በመፍትሔ ከጠፋ ወደ ቀዶ ህክምና ወደ ከባድ ህክምናዎች ማምራት እንደሚገባ መክረዋል።
ጤናዎትን ይጠብቁ












Comments