ምጣኔ ሐብት - ሐምሌ 7 2017 - የኢንተርኔት ኢኮኖሚ ምንድን ነው ?
- sheger1021fm
- Jul 15
- 1 min read

ኢንተርኔት ፤ ከጀርባው ያለው በባህር ውቅያኖስ የተዘረጋው የፋይበር ገመድ ሰብመሪን ኬብል ( submarine cable) ስራው ምንድነው?
በየብስ በምድር ፤ በየትኛውም ስፍራ የተቀበረው ይህ የግሎባል ጥልፍል ገመድ ለ ኢኮኖሚው ምን ማለት ነው?
በዚህ ሰዓት በዓለም ከተሰማራው ወይም በዚህ ምድር ላይ እንዲኖር ከተፈቀደለት 5.5 ቢሊየን የሚሆነው ህዝብ እጁ ላይ ባለው በአይነት አይነቱ ስልክ ጋር ተጣምዷል።
ይህ ከዲጅታል ወይም ኢንተርኔት ኢኮኖሚው ጋር ምን አስተሳሰረው?
ይህው ህዝብ በዚህ ሰዓት እጁ ላይ ባለው ስልክ በኢንተርኔት ተሳስሯል።
በ ኢ - ኮሜርስ ም ሆነ በሌላ በትልልቅ ፋይናንስ ቤቶች በባንክ ሳይቀር በ ኢንተርኔት አማካኝነተእ ግዙፍ ገንዘብ እየተሽከረከረ ነው።
አንቱ የተባሉ የዓለሚቱ ግዙፍ ተቌሞች በበይነ መረብ እየታገዙ ከደንበኞቻቸውጋ ገቢ ወጭ ንግዱን እያጧጧፋት ነው።
ይህ የኢንተርኔት ኢኮኖሚ ይባላል።
ለመሆኑ የዓለም ሐገሮች አይናቸውን ጥለው የሚከታተሉት ይህ የበይነ መረብ አለም ኢኮኖሚ ከጀርባው ምን አለ?
አቶ አለም ኃይለ ማርያ የኔትዎርክ ኢንፍራስትራክቸር ባለሙያ ናቸው፤ እሳቸው አሁን በኢትዮ ቴሌኮም ዲፕዩቲ ቺፍ ኢንፍራስትራክቸር ኦፊሰር ናቸው ።
አቶ ዓለም ለዚህ ማብራሪያ አላቸው።
ተህቦ ንጉሴ








