top of page

ሚያዝያ 28 2017 - የገቢዎች ሚኒስቴር ከአምናው የ279 ቢሊዮን ብር ብልጫ ያለው ገቢ ሰበሰብኩ አለ

  • sheger1021fm
  • May 6
  • 1 min read

የገቢዎች ሚኒስቴር ከአምናው የ279 ቢሊዮን ብር ብልጫ ያለው ገቢ ሰበሰብኩ አለ፡፡


ባለፉት 9 ወራት ከግብር እና ከተለያዩ የገቢ ምንጮች ከ646 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን በሪፖርቱ ተናግሯል፡፡


ገቢው ከአምናው ተመሳሳይ ጊዜ 74 በመቶ ወይም የ279 ቢሊየን ብር ብልጫ ያለው ነው ተብሏል፡፡


ከተሰበሰበው ገቢ 345.9 ቢሊየን ብሩ ከታክስ የተገኘ ሲሆን ከወጭ ንግድ ቀረጥና ታክስ ደግሞ 307.2 ቢሊየን ብር ተሰብስቧል ይላል የገቢዎች ሚኒስቴር የ9 ወር ሪፖርት፡፡


ገቢው በመቶ ቢሊዮኖች ከአምናው ከፍ ያለበት ምክንያት ግን በሪፖርቱ አልተብራራም፡፡


በሌላ በኩል ህገ-ወጥ ንግድ፣ ገቢን መደበቅ፣ ግብይትን ያለ ደረሰኝ መከወን፣ ግብር ስወራና ታክስ ማጭበርበር አሁንም ፈተና ሆነውብኛል ብሏል ሚኒስቴር መ/ቤቱ፡፡

ree

ተሰውሮብኝ ነበር ያለውን ገቢ ለማግኘትም በድንገተኛ ፍተሻ፣ በሒሳብ ምርመራ ወይም ኦዲትና መሰል ስራዎች የህግ ማስከበር ስራ ሰርቻለሁ ብሏል፡፡


በዚህም 7,583 የሒሳብ መዝገቦችን ኦዲት አድርጌ ከነወለድና፤ መቀጫው ከ60 ቢሊዮን ብር በላይ እንዲከፍሉም ተወስኗል ተብሏል፡፡


የታክስ ማጭበርበር ፈፅመዋል የተባሉ 641 ድርጅቶችም ተለይተው ሒሳባቸው ተመርምሯል ያለው ሚኒስቴሩ ከ235 ድርጅቶች የ3.4 ቢሊየን ብር ዋጋ ያላቸው ሐሰተኛ የግዥ ደረሰኞችን ይዣለሁ ሲል በሪፖርቱ አስፍሯል፡፡


በሌላ በኩል 19 ድርጅቶች ከ5 ቢሊየን ብር መቀበሉን በላይ ታክስ ሊከፍልበት የሚገባን ገቢ ደብቀው ተገኝተዋልም ተብሏል፡፡


ግብይት ሲፈፅሙ ደረሰኝ ሳይቆርጡ የተያዙ 597 ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በወንጀል ምርመራና በክስ ሂደት ላይ በተጨማሪም በኦዲት ምርመራ የተለያዩ 584 ድርጅቶችን ኦዲት በማድረግ ወለድና መቀጫን ጨምሮ 25.8 ቢሊየን ብር እንዲከፍሉ እንደተወሰነባቸው ከሪፖርቱ ተመልክቷል፡፡


በአጠቃላይ በመደበኛና በምርመራ ኦዲት በሂሳብ መዝገባቸው ያልተገባ ኪሳራ ካቀረቡ ድርጅቶችም 26.2 ቢሊየን ብር መቀበሉን፣ ተመላሽ ይደረግልን ብለው ከጠየቁ ደግሞ 2.6 ቢሊየን ብር ማስቀረት ችያለሁ ሲል የገቢዎች ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡


ሌላው ሚኒስቴር መ/ቤቱ ፈተና ሆኖብኛል ባለው የኮንትሮባንድ ንግድም ባለፉት 9 ወራት 15.6 ቢሊየን ብር የተገመቱ ገቢና ወጭ የኮንትሮባንድ እቃዎች ተይዘዋል ብሏል፡፡


ትዕግስት ዘሪሁን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…






Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page