top of page

ሚያዝያ 23 2017 - ''የግል የሎጀስቲክስ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሚያነሱትን ጥያቄ ለመመለስ እየሰራሁ ነው'' የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚ/ር

  • sheger1021fm
  • May 1
  • 1 min read

የወጪ ንግድ ገቢን ለማቀላጠፍ፤ የግል የሎጀስቲክስ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሚያነሱትን ጥያቄ ለመመለስ እየሰራሁ ነው ሲል የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ተናገረ፡፡


የመንግስትና የግሉ የሎጀስቲክስ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ዘርፉን ለማቀላጠፍ በጋራ መስራት እንዳለባቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተናግሯል፡፡

ree

እነዚህ የግሉ የሎጀስቲክስ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሚያነሱ ጥያቄ ቢኖርም ችግሩ መፍትሄ እንዲያገኝ በጋራ መስራቱ የሚበጅ ነው ተብሏል፡፡


በዘርፉ ረጅም ዓመት ያስቆጠሩ ተቋማት እንዳሉ ሁሉ ለአዳዲሶቹ ድርጅቶችም እየሰሩ ላሉት ስራ እውቅና መስጠት እንደሚያስፈልግ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር ዴኤታ ደንጌ ቦሩ ተናግረዋል፡፡


በግሉ ዘርፍ እያቀላጠፉ ያሉ ተቋማት ከፖሊሲ አኳያ የፋይናንስና የመሬት አቅርቦት ችግር ካለ ለመፍታት ዝግጁነን ሲሉ ሚኒስቴር ዴኤታው አስረድተዋል፡፡


ኢትዮጵያ በአፍሪካ የነፃ ንግድ ቀጠና ላይ ምርቶቿን ይዛ ለመሳተፍ የግሉና የመንግስት አገልግሎትን ማቀላጠፍ አስፈላጊ ነው ተብሏል፡፡


ይህ ደግሞ በመንግስት ብቻ የሚሸፍን ባለመሆኑ የግሉን ዘርፍ በማሳተፍ ጥያቄዎቻቸውን በመመለስ ስራውን ማስቀጠል እንደሚያስፈልግም ተነግሯል።


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…. https://www.mixcloud.com/ShegerFM/frger/


ማርታ በቀለ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…






Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page