ሚያዝያ 23 2017 - ''ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል አለመወሰኑ በኢንዱስትሪ ፓርኮች እና በተለያዩ ፋብሪካዎች የሚሰሩ የሠራተኞች ላይ ችግር ፈጥሯል'' ኢሰመኮ
- sheger1021fm
- 1 day ago
- 1 min read
ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል አለመወሰኑ በኢንዱስትሪ ፓርኮች እና በተለያዩ ፋብሪካዎች የሚሰሩ የሠራተኞች ላይ ችግር ፈጥሯል ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ተናገረ፡፡
በአዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ሸገር ሲቲና ሃዋሳ ከተሞች በሚገኙ ኢንደስትሪ ፓርኮችና ፋብሪካዎች ውስጥ ተቀጥሮ የሚሰሩ የሴት ሰራተኞች መብቶች አያያዝን በተመለከተ ከሚመለከታቸው ጋር ዉይይት አድርጓል፡፡
ኮሚሽኑ በዚህ ጉዳይ ሶስት ዙር ክትትል ማድረጉን በዚህም የተሻሻሉና የቀጠሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን አግኝቻለሁ ብሏል፡፡
በጤና አጠባበቅ ዙሪያ የግብዓቶች አለመሟላት፣ የደመወዝ ጉዳይ፣ የፀረ ትንኮሳ ፖሊሲ አለመኖርና ሌሎችም የቀጠሉ ናቸው መባሉንም ሰምተናል፡፡
በአሰሪና ሰራተኛ አዋጁ ላይ ያሉ መብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ክፍተቶች መታየታቸውን ተነግሯል፡፡
ይህም ሆኖ መሻሻል የታየባቸው ጉዳዮች እንዳሉም ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ሰምተናል
ሴቶች የወሊድ ጊዜ እረፍት ከክፍያ ጋር ማግኘት ሲገባቸው ይህ መብት ሳይረጋገጥ መቅረቱንም ኢሰመኮ ተመልክቻለው ብሏል፡፡

ከሁሉም በላይ አሳሳቢው ደግሞ መንግስት ዝቅተኛ የሆነ የደመወዝ ወለል ባለመወሰኑ ችግር ያመጣል ሲሉ የተናገሩት የኢሰመኮ የሴቶች፣ የህፃናት፣ የአረጋዊያንና የአካል ጉዳተኞች መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገ/ሐዋርያ ናቸው፡፡
ሌላኛው አሳሳቢ ጉዳይ በሀዋሳ እና በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች በሁሉም ፋብሪካዎች የአደጋ መከላከያዎች እና የጤና መጠበቂያ ቁሳቁሶች በበቂ ሁኔታ አለመሟላታቸው ነው ብሏል፡፡
የጸረ ጾታ ትንኮሳ ፖሊሲው ባለባቸው ፋብሪካዎችም ቢሆን ሰራተኞች በቂ የሆነ እውቀት አለመያዛቸውን ነግረውና፡፡
ኮሚሽኑ በመጀመሪያው፣ በሁለተኛ በሶስተኛው ዙር ክትትል ካስቀመጣቸው ምክር ሀሳቦች ተተግብረው ያገኛቸውና መሻሻል የታየባቸውን ጉዳዮች በውይይቱ ተመልክቻልሁ ብሏል፡፡
የሰራተኞች ማህበራት በሁሉም ፋብሪካዎች መቋቋማቸው አንዱ ማሳያ ነው ተብሏል፡፡
ኢሰመኮ ይህን ከተመለከተ በኋላ አሁንም በቀጣይ መሻሻል አለባቸው ባላቸው ጉዳዮች ላይም ምክረ ሃሳቡን አስቀምጧል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…. https://www.mixcloud.com/ShegerFM/regyer/
ማርታ በቀለ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
Comments