top of page

ሚያዝያ 22 2017 - የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት በግሉ ዘርፍ እንዲመራ ለማድረግ እየተሰራ እንደሆነ የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ተናገሩ

  • sheger1021fm
  • 1 day ago
  • 1 min read

የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት በግሉ ዘርፍ እንዲመራ ለማድረግ እየተሰራ እንደሆነ የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ተናገሩ፡፡


ከንቲባዋ ይህን የተናገሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን በዛሬው እለትባካሄደበት ወቅት ነው፡፡


ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የምክር ቤት አባላት የዋጋ ንረትን በተመለከተ ላቀረቡላቸው ጥያቄ ምላሽ በሰጡበት ወቅት ዋጋ ንረቱ በማህበረሰቡ ላይ ጫና እንዳያሳድር የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ እንዳሉ ተናግረዋል፡፡


ከነዚህም ውስጥ በአራቱም የከተማዋ መግቢያዎች ያለምንም ኬላ ምርቶች እንዲገቡ እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰው ከተሞች ሸማቾች ብቻ ሳይሆን አምራቾች እንደሆኑም እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

ሌላው የዋጋ ንረቱን ለመቀነስ ማህበረሰቡን እየደጎምን ነው ብለዋል ከንቲባዋ፡፡


በትራንስፖርት ብቻ የከተማዋን ኗሪ በየዓመቱ ከ3 ቢሊዮን በላይ እያወጣን እየደጎምን ነው ያሉት ወይዘሮ አዳነች በተለይ ቀላል ባቡር ወደ አዲስ አበባ ከመጣ ወዲህ ወጪው ቀላል እንዳይመስላቸው ብለዋል፡፡


የከተማዋ አውቶብሶች ከሚሰጡት አገልግሎት የሚገኙት ገቢ መስሪያ ቤታቸውን እንዳማያስተዳደር የጠቆሙት ከንቲባዋ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ዋና ዓላማውን ሳይስት ማህበረሰቡ ላይ ጫና ሳይፈጥር በግሉ ዘርፍ የሚመራበትን ሂደት እየሞከርን ነው ብለዋል፡፡


ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…






Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page