ሚያዝያ 22 2017 - እናት ባንክ “ለእናቴ” የፅሁፍ ውድድር ከአዕምሯዊ ጥበቃ ባለስልጣን የባለቤትነት ማረጋገጫ ማግኘቱን ተናገረ፡፡
- sheger1021fm
- Apr 30
- 1 min read
እናት ባንክ ከአምና ጀምሮ እያካሄደ ያለው “ለእናቴ” የፅሁፍ ውድድር ከአዕምሯዊ ጥበቃ ባለስልጣን የባለቤትነት ማረጋገጫ ማግኘቱን ባንኩ ተናገረ፡፡
“ለእናቴ” የፅሁፍ ውድድር ሰዎች ስለ እናቶቻቸው ጊዜ ሰጥተው እንዲያስቡ፣ እንዲፅፉ እና ተወዳድረው እንዲሸለሙ የሚያደርግ የእናት ባንክ ፕሮግራም ነው፡፡
ይህ የፅሁፍ ውድድር ትላንት ምሽት ለሁለተኛ ጊዜ ተካሂዷል፡፡
በውድድሩ አንደኛ ለወጣው 150 ሺህ ብር፣ ሁለተኛ ለወጣችው 125 ሺህ፣ ሶስተኛ ለወጣው ደግሞ 100 ሺህ ብር ተሸልመዋል፡፡

አራተኛ ለወጣው 75 ሺህ ብር እንዲሁም አምስተኛ ለወጣው ደግሞ 50 ሺህ ብር ተሸልመዋል፡፡
ከ1ኛ እስከ 5ኛ የወጡ ተወዳዳሪዎች የተወዳሩበት ፅሁፍ መፅሄት ላይ ታትሞላቸዋል፡፡

የዓመቱ ድንቅ እናት በሚልም ወ/ሮ የኔነሽ ፍሪሳ መርደሳ የተባሉ እናት የተመረጡት ሲሆን የ200 ሺህ ብር የእናት ባንክ አክሲዮን ተሰጥቷቸዋል፡፡
ይህ የእናት ባንክ ለእናቴ ሲል የጠራውና ትናንት ምሽት ለሁለተኛ ጊዜ የተካሄደው ፕሮግራም የባለቤትነት ማረጋገጫ እንዳገኘ የባንኩ ፕሬዘዳንት አቶ ኤርሚያስ አንዳርጌ አስረድተዋል፡፡
ይህም ውድድር መካሄዱን እንዲቀጥል ያግዛል ብለዋል፡፡
ውድድሩ እናትነት መግለፅ መሆኑንን ያስረዱት ፕሬዘዳንቱ በዚህም "የውድድሩ ተሳታፊዎች እናትነትን ከፍ ስላደረጋችሁ አመሰግናለሁ" ብለዋቸዋል፡፡
እናት ባንክ የሴቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተለያዩ መላዎች ስራ ላይ ማዋሉን አስረድቷል፡፡

ከእነዚህ መካከልም ከባንኩ አጠቃላይ ትርፍ ከ3 እስከ 5 በመቶ እየተቀነሰ ማስያዣ ማቅብ ለማግይችሉ ሴቶች ብድር እንደሚሰጥ ተናግሯል፡፡
ባንኩ ቅርንጨፎቹንም የሚሰይመው ለሀገራቸው እና ለሴቶች የጎላ ስራ በሰሩ ሴቶች ሰም እንደሆነ አስታውሶ በቅርቡም ሁሉንም እናቶች የሚወክል “እማዬ” የተሰኘ ቅርንጫፍ መክፈቱ ይታወሳል፡፡
ንጋቱ ሙሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r












Comments