top of page

ሚያዝያ 20 2017 - በትግራይ ክልል የተጋነነ የነዳጅ እጥረት በመኖሩ ተዘዋውሮ ለመስራት መቸገሩን የእምባ ጠባቂ ተቋም ተናገረ

  • sheger1021fm
  • Apr 28
  • 1 min read

በትግራይ ክልል የተጋነነ የነዳጅ እጥረት በመኖሩ ተዘዋውሮ ለመስራት መቸገሩን የእምባ ጠባቂ ተቋም የመቀሌ ቅጫፍ ፅህፈት ቤት ተናገረ፡፡


ከተቋሙ እንደሰማነው በጥቁር ገበያ ነዳጅ ከመደበኛ ዋጋው እስከ ሁለት እጥፍ ይሸጣል፤ሌሎች ተቋማት እንዲሁም ነዋሪው ለመንቀሳቀስ ተቸግሯል ተብሏል፡፡


በትግራይ ክልል ያለው #የነዳጅ_እጥረት እየተባባሰ መምጣቱን የሚናገረው ፅህፈት ቤቱ ይህ ችግር በክልሉ ተዘዋውሮ ለመስራት እንቅፋት ሆኖብኛል ብሎናል፡፡


ይሁንና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በክልሉ ባሉ ማደያዎች ነዳድ ማግኘት ብር እሆነ ነው፤ነዳጅ ሰወር ብሎ በጥቁር ገበያ ከመደበኛ ዋጋው እስከ ሁለት እጥፍ እየተሸጠ ነው፤የትራንስፖርት ዋጋውም በዚያው የሚጠየቀው ከነበረው በ1እና2 እጥፍ ሆኗል፤ እኛ የፌድራል ተቋም እንደመሆናችን ሂሳብ የምናወራርደው በመደበኛ ዋጋው ነው፤የግድ ስራውን መስራት ስላለብን ለትራንስፖርት የምናወታው በእጥፍ ነው ያሉን የቅርጫፍ ፅህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ፀሃዬ እምባዬ ናቸው፡፡


ባልተመቸ ሁኔታ ውስጥም ቢሆን የአስተዳደር በደል ደረሰብን፤እምባችን ይታበስልን የሚሉ አቤቱታ አቅራቢዎችን እያስተናገድኩ ነው የሚለው የኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም የመቀሌ ቅርጫፍ ፅህፈት ቤት፤ በክልሉ ባለፉት 9 ወራት ከቀረቡ 135 አቤቱታዎች መካከል 42ቱ ወቅሬታቸው መፍትሄ አግኝቶ እምባቸው ታብሷል፤ ከቀረቡት መካከል 93ቱ ተቀባይነት የላቸውም እኛን የሚመለከቱ ጉዳዮች ናቸው ብለን መልሰናቸዋል ብለውናል፡፡


የመጣ ቅሬታን ሁሉ አንቀበልም እናጣራለን የሚሉት አቶ ጸሃዬ በዚህም ደረጃቸውን ያልጠበቁ አቤቱታዎች ተብለው የተመለሱት 61ቅሬታዎች መሆናቸውንና ነግረውናል፡፡


አንድ ተበዳይ ወደ እምባ ጠባቂ ተቋም ለመምጣት በዳዩን አካል በማነጋገር መልስ ያጣ መሆን እንዳለበትም ጠቅሰዋል፡፡


በክልሉ ያለው የነዳጅ እጥረት አላሰራ ብሎኛል የሚለው ተቋሙ የሚመለከታቸው ጉዳዩን ተመልክተው የእርምት እርምጃ እንዲወስዱም ጠይቋል፡፡


ስለጉዳዩ ምላሽ እንዲሰጡን የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣንን ለማነጋገር በተደጋጋሚ ብንሞክርም ለጊዜው ምላሻቸውን ማግኘት አልቻልንም፡፡


በሌላ በኩል ከዚህ ቀደም በትግራይ ክልል በሁለት ከንቲባዎች ይተዳደሩ የነበሩ ከተሞች አዲሱ አመራር ከተሸመ ወዲህ ወደ አንድ መምጣታቸው ስራችንን አቅልሎታልም ብለዋል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…. https://www.mixcloud.com/ShegerFM/dfvgdg/


ምንታምር ፀጋው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…






1 Comment


borubond
Apr 29

እውነት ኀው ሸገር ሬድዮ በተለየ አቀራረብ የሬድዮ መደመጥን ተፈላጊነት ሳቢና ማራኪ አድርጎ እያገለገለ ነው ብዬ እመሠክራሁ ።

Like
Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page