top of page

ሚያዝያ 18 2017 - የባህር ማዶ ወሬዎች

  • sheger1021fm
  • Apr 26
  • 2 min read

በሳምንቱ መጀመሪያ ከዚህ አለም በሞት የተለዩት የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አባ ፍራንስስ የቀብር ሥነ ሥርዓት ዛሬ ይፈፀማል፡፡


አባ ፍራንሲስ በአንጎል ውስጥ የደም መፍሰስ እና በልብ ድካም በ88 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት የተለዩት ባለፈው ሰኞ ነው፡፡


እጅግ በርካታ ካቶሊካውያን በቫቲካን በአባ ፍራንሲስ ሕልፍት ሐዘናቸው ሲገልጹ ሰንብተዋል፡፡


የአባ ፍራንሲስ የቀብር ሥነ ሥርዓት ዛሬ በሮም ቅድስተ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ይፈፅማል፡፡

የአሜሪካውን ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕን ጨምሮ የ50 አገራት መሪዎች በርዕሰ ሊቀ ጳጳሱ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ እንደሚገኙ ታውቋል፡፡


ከአለም አቀፍ ድርጅቶች መሪዎች መካከል የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝም የሥነ ሥርዓቱ ተካፋይ ናቸው ተብሏል፡፡


ቀጣዩ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በቤተ ክርስቲያኒቱ ካርዲናሎች በዝግ በሚከናወን ሥነ ሥርዓት እንደሚመረጡ መረጃው አስታውሷል፡፡



የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሩሲያ እና ዩክሬይን የሚያሂዱትን ጦርነት ለማስቆም ወደ ስምምነት እየተቃረቡ ነው አሉ፡፡


ቀደም ሲል ትራምፕ ሁለቱ አገሮች በብዙ የጦርነት ማስቆሚያ ጉዳዮች ላይ መስማማታቸውን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ማስፈራቸውን ቢቢሲ አስታውሷል፡፡


የዩክሬይኑ ፕሬዘዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ ትናንት በቪዲዮ ተቀርፆ በተላለፈ መልእክታቸው ለተሟላ የተኩስ አቁም በሩሲያ ላይ ጫና እንዲበረታባት መጠየቃቸው ተጠቅሷል፡፡


እንደሚባለው ድርድሩ የግዛት ሽግሽግንም ይጨምራል፡፡


አሜሪካ የክራሚያ ልሳነ ምድር ለሩሲያ እንዲፀናላት የሚጠይቅ ሀሳብ ማቅረቧ ሲነገር ሰንብቷል፡፡


ቀደም ሲል የዩክሬይን መሪዎች ለሩሲያ ስንዝር መሬት አንተውላትም ሲሉ እንደነበር መረጃው አስታውሷል፡፡



በጋቦኑ ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ የአገሪቱ ወታደራዊ መሪ ብሪስ አሊጉ ንጉየማ ማሸነፋቸው በህገ መንግስታዊው ፍርድ ቤት ፀደቀላቸው፡፡


ንጉየማ ለፕሬዘዳንታዊ ምርጫው ከተሰጠው ድምፅ 95 በመቶ ያህሉን በማግኘት ማሸነፋቸው ሲነገር መሰንበቱን አናዶሉ ፅፏል፡፡


ሕገ መንግስታዊው ፍርድ ቤት ደግሞ ውጤቱን ተቀብሎ ማፅደቁ ተሰምቷል፡፡


ወታደራዊ መሪው ቀደም ሲል የአገሪቱ ጊዜያዊ ፕሬዘዳንት ተደርገው ነበር፡፡


በምርጫው ውጤት መሰረት ከእንግዲህ አገሪቱን በፕሬዘዳንትነት ለ7 አመታት እንደሚመሩ ታውቋል፡፡


ንጉየማ ወደ አገር መሪነቱ የመጡት ከአመት ከ8 ወራት በፊት የቀድሞው ፕሬዘዳንት ዓሊ ቦንጎን አስተዳደር በወታደራዊ ግልበጣ በማስወገድ መሆኑ ይታወቃል፡፡



የዓለም የምግብ ፕሮግራም በጋዛ ሰርጥ የእርዳታ የምግብ ክምችቴ ተሟጧል አለ፡፡


የድርጅቱ መጋዘኖች ወና የሆኑት እስራኤል ወደ ጋዛ ሰርጥ የእርዳታ ምግብም ሆነ ሌሎች መሰረታዊ ነገሮች እንዳያፉ በመከልከሏ ምክንያት እንደሆነ ታውቋል፡፡


እስራኤል ወደዚህ ክልላ ከገባች ከወር በላይ ሆኖታል፡፡


ይም በጋዛ ሰብአዊ ቀውሱን እያባባሰው መሆኑ በድርጅቱ መረጃ ተመልክቷል፡፡


የወደፊቱ ደግሞ ከዚህም በላይ በእጅጉ አሳሳቢ ነው ተብሏል፡፡


ለፍልስጤማውያን ሰብአዊ እርዳታ በማቅረብ የሚታወቀው የተባበሩት መንግስታት አካል /አንሩዋ/ እስራኤል ፍልስጤማውያንን በሰው ሰራሽ ረሃብ እየቀጣቻቸው ነው በሚል ተቃውሞውን አሰምቷል፡፡


የአለም የምግብ ፕሮግራም ወደ ጋዛ ሰብአዊ እርዳታ እንዳያልፍ መከልከሉን በዝምታ ሊያልፈው አይገባም ማለቱ ተጠቅሷል፡፡


የኔነህ ከበደ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…






コメント


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page